ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በኬንያ ጉብኝት እንዲያደርጉ ከፕሬዚዳንት ኡሁሩ ግብዣ ቀረበላቸው
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኬንያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እንዲያደርጉ ግብዣ ቀረበላቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞኒካ ጁማን በዛሬው እለት በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
በውይይታቸውም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሞኒካ ጁማ ከኬንያው ፕሬዚዳንት የተላከውን የደስታ መግለጫ እና የኬንያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ግብዣ ደብዳቤን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስረክበዋል።
በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዶክተር አብይ አህመድን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ የደስታ መግለጫ ልከው እንደነበረ ይታወሳል።
ፕሬዚዳንት ኡሁሩ በመግለጫቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር የሀገራቱን የጋራ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ መስኮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት ያላቸውን ፍላጎትንም ገልፀዋል።
በተለይም ሀገራቱ ቀጣናዊና አህጉራዊ ሰላምና ደህንነትን በማረጋገጥ ልማትን ለማምጣት በሚያደርጉት ጥረት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸውም ጠቅሰዋል።
ኤፍ.ቢ.ሲ
Share your thoughts on this post