fbpx
AMHARIC

ገጣሚዎችና ሞዴሊስቶቹ ለመጀመሪያ ጊዜ በስደተኞች ጣቢያ ስራቸውን አቀረቡ

ለስደተኞች የሚሰጠውን የተሳሳተ አመለካከት ለመቀየር ሲባል ታዋቂ ገጣሚዎችና ሞዴሊስቶች በሰሜናዊ ኬንያ በሚገኘው የካኩማ ስደተኞች ጣቢያ ተገኝተው የጥበብ ስራዎቻቸውን በማቅረብ አዲስ ታሪክ ማጻፋቸው ተገለጸ፡፡

ለስደተኞች እነዚህ የጥበብ ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን ለስደተኞች በመጠለያ ጣቢያ ሲያቀርቡ በዓለም የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡

የካኩማ የስደተኞች ጣቢያ ከ180 ሺህ በላይ ስደተኞች የሚያኖር ሲሆን በአጫጭር የፊልም ስራዎቻቸው ከንግድ፤ ቴክኖሎጂ እስከ አካባቢ ጥበቃና ሰብዓዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ለስደተኞቹ አቅርበዋል ነው የተባለው፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በበኩሉ ስደተኞች በተጠለሉበት ሀገርና አካባቢ የሚገጥማቸውን ችግር ለማሳየትና የተሰጣቸውን ትክክለኛ አመለካከት ለመቅረፍ ርዳል ብሏል፡፡

በእንደዚህ ዓይነቱ ዝግጅቶች ስደተኞች ምን እንደሚያስፈልጋቸው መግለጽ ብቻ ሳይሆን እጅጉን ልዩ የሆነ ተሰጥኦ እንዳላቸው ለማስተዋወቅም እንደሚረዳ ነው የተገለጸው፡፡

የሶማሊያ፤ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ደቡብ ሱዳናዊያን ስደተኞች በብዛት በካኩማ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ሲሆን ህይወታቸውን በአዲስ መልክ ለመምራትም እውቀት ቀስመዋል ነው የተባለው፡፡

የግጥም ስራዎቻቸውን ካቀረቡ ገጣሚያን መካከልም ሪያ ዊሊያም፤ አትሌት ፑር ቤይል፤ መምህርት ሜሪ ኒይሪያክ፤ የኮንጎው ፊልም ሰሪዋ አሚና ርዋኖ እና ኤሚ ማህሙድ እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

ከሞዴሊስቶች ደግሞ የሶማሊያና አሜሪካ ዜግነት ያላት ሃሊማ ኤደን አንዷ ስትሆን በካኩማ የስደተኞች ጣቢያ ተወልዳ ማደጓ ደግሞ የችግሩን መጠን በቅጡ እንድታውቅ እንደረዳት ተነግሯል፡፡

ሮይተርስ

 

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram