fbpx
AMHARIC

ድምጽ በበዛበት አካባቢ የሚሰሩ ሰዎች ለከፍተኛ የደም ግፊትና ኮለስትሮል መጠን ተጋላጭ ናቸው- ጥናት

ድምጽ በበዛበት አካባቢ ስራቸውን የሚያከናውኑ ሰዎች ለከፍተኛ የደም ግፊትና የኮለስትሮን መጠን መጨመር ተጋላጭ እንደሚሆኑ የአሜሪካ ተመራማሪዎች ይፋ አድርገዋል፡፡

ከዚህ በፊት ይፋ የተደረጉት ጥናቶች ከፍተኛ ጩኸት ያላቸው ድምፆች የመስማት ችግርን እንደሚያስከትሉ ቢሆንም የአሁኑ ጥናት ግን ከልብ ህመም ጋር ተያያዥነት እንዳለውም ነው የተነገረው፡፡

ከ22 ሺህ በላይ ከፍተኛ የድምጽ ጩኸት ባለበት አካባቢ በመሰሩ ግለሰቦች ላይ በተደረገ ጥናት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የመስማት ችግር፤ ከፍተኛ የደም ግፊትና የኮለስትሮል መጠን ተጋላጭ ሆነዋል፡፡

በአሜሪካ ከ22 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከፍተኛ የድምጽ ጩኸት በሚኖርበት አካባቢ ስራቸውን እንደሚያከናውኑ ነው የተገለጸው፡፡

የድምጽ መጠንን ለጤንነት ስጋት በማይሆንበት ደረጃ ላይ መቀነስ ከተቻለ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ሊገጥማቸው የሚችለውን የጤና ቀውስ ሊቀርፍ ይችላል፡፡

ከፍተኛ የደምጽ መጠን በሰዎች ላይ ጭንቀትን ስለሚፈጥር ከልብ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የጤና እክሎችን ሊፈጥር እንደሚችል ነው ጥናቱ ይፋ ያደረገው፡፡

በመሆኑም እንደ ማዕድን ምርት፤ ማምረቻ ፋብሪካዎችና ግንባታ አካባቢ የሚሰሩ ሰዎች ነጉዳዩ ትኩረት በመስጠት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡

ምንጭ፡ ሮይተርስ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram