fbpx
AMHARIC

ደቡብ ሱዳን የፕሬዚዳንቱን የስልጣን ዘመን ለማራዘም የሚያስችል የህገ መንግስት ማሻሻያ አዘጋጀች

የደቡብ ሱዳን መንግስት የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርን የስልጣን ዘመን ለማርዘም የሚያስችል ረቂቅ የህገ መንግስት ማሻሻያ ማዘጋጀቷ ተሰማ።

የሀገሪቱ መንግስት ያቀረበው የህገ መንግስት ማሻሻያ የፕሬዚዳንቱን የስልጣን ላይ ቆይታ በሶስት ዓመት የሚያራዝም መሆኑም ተነግሯል።

የደቡብ ሱዳን ፓርላማም በቀረበለት የህገ መንግስት ማሻሻየ ላይ ክርክር መጀመሩ ታውቋል።

የሀገሪቱ የፍትህና የህገ መንግስት ጉዳዮች ሚኒስትር ፓውሊኖ ዋናዊላ ለሀገሪቱ ብሄራዊ የሽግግር ህግ አውጪ ምክር ቤት በማሻሻያው ዙሪያ ራሪያ ሰጥተዋል።

የህገ መንግስት ማሻሻያው የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር፣ የምክትላቸው እና የሀገሪቱ ፓርላማን ቆይታን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር እስከ 2021 የሚያራዝም መሆኑንም ታውቀዋል።

የደቡብ ሱዳን ብሄራዊ የሽግግር ህግ አውጪ ምክር ቤት በማሻሻያው ላይ ይመክራል የተባለ ሲሆን፥ ከተወያየ በኋላም ለማሻሻያው ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

አዲሱ የህገ መንግስት ሻሻያ ረቂቅ ለሀገሪቱ ፓርላማ ቀርቦ ከፀደቀም ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ለተጨማሪ ሶስት ዓመታት ሀገሪቱን እንዲመሩ እድል ይሰጣቸዋል ተብሏል።

 

ምንጭ፦ africa.cgtn.com

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram