fbpx
AMHARIC

ያለጊዜ መውለድ ስጋትን በደም ምርመራ ማወቅ እንደሚቻል አንድ ጥናት አመላከተ

አንዲት ነፍሰጡር ያለጊዜዋ መውለድ ያለመውለዷን በደም ናሙና ምርመራ መተንበይ እንደሚቻል አዲስ ጥናት ማመላከቱን ዘ ጋርዲያን ዘገበ፡፡

ከነፍሰጡሩዋ የተወሰደውን የደም ናሙና ምርመራ በማድረግ የጽንሱን ዕድሜ እና ያለጊዜ የመውለድ ስጋት መኖሩን ማረጋገጥ እንደሚቻል ጥናቱ አመላክቷል፡፡

ጥናቱ የተከናወነው በጥቂት በጎ ፈቃደኞች ላይ በመሆኑ የተሟላ መረጃ ነው ማለት እንደማይቻል ጥናቱን ያከናወኑት ተመራማሪዎች አስታውቀው፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥልቅ የቤተሙከራ ፍተሻ በማድረግ ስራቸውን ይፋ እንደሚያወጡ ተናግረዋል፡፡

ጥናቱ አሁን ባለበት ደረጃ ከ31 ነፍሰጡር ሴቶች ላይ በየሳምንቱ ናሙና በመውሰድ የሚያስከትለውን ለውጥ መፈተሽ ተችሏል ፡፡

ግኝቱንም አዳዲስ ጥናቶች በሚታተሙበት የሳይንስ ጆርናል ላይ በማውጣት ምርምሩ ያለበትን ደረጃ ቡድኑ አስታውቋል፡፡
ያለጊዜ በሚወልዱ ሴቶች ላይ ክትትል የሚያደርገው የአሜሪካው ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ አባል ዶ/ር ማድስ ሜልቢ ጥናቱን አስመልክተው ሲናገሩ ‹‹ ወደመጨረሻው ውጤት ከመምጣታችን በፊት በመስኩ ሠፊ ጥናት ማድረግ ይኖርብናል፡፡ከዚህ በኋላ ብቻ ነው ወደመፍትሔው የምንሸጋገረው ››ብለዋል፡፡

የቅዱስ ቶማስ ሆስፒታል ክሊኒካል ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አንድሪው ሼናን በበኩላቸው ‹‹ምንም እንኳ በምርምሩ ላይ የተሳተፉ ሴቶች ቁጥር አነስተኛ ቢሆንም የተገኘው ውጤት አመርቂ ነው ››ብለዋል፡፡

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram