fbpx
AMHARIC

የ30 ዓመቷ የቦትስዋና ሚኒስትር በአፍሪካ ማህበራዊ ድረ ገጾች እየተደነቀች ነው

በቦትስዋና አዲስ ለተመረጠችው የ30 ዓመቷ ሚኒስትር ቦጎሎ ጆይ ክኔዌንዶ በርካታ የማህበራዊ ድረገጽ ተጠቃሚዎች አድናቆት በመቸር ልምዱ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ሊለመድ እንደሚገባ አጽንኦት እየሠጡ ይገኛሉ፡፡

አዲሱ የቦትስዋና ፕሬዝዳንት ሞክግዊጺ ማሲሲ በበዓለ ሲመታቸው ወቅት ወጣቶችን እንደሚያበረታቱ በገለጹት መሠረት በዕድሜ አነስተኛዋ ክኔዌንዶን በሚኒስትርነት ሠይመዋል፡፡
ክኔዌንዶ በተሰናባቹ ሚኒስትር ካማ የፓርላማ አባል ሆና ያገለገለች ስትሆን አሁን የኢንቨስትመንት ፣ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ሆና መሾሟን አፍሪካ ኒውስ ይፋ አድርጓል፡፡

ተሿሚዋ ቀደም ብላ በጋና መንግስት ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ውስጥ የንግድ ኢኮኖሚስት ሆና ያገለገለች ስትሆን በሃገሯ ቦትስዋና ሞላያ ክጎሲ የተባለ አመራርና ክህሎት የሚያሠርጽ ፕሮግራም ከፍታ ለበርካታ ወጣት አፍሪካውያን ሴት አመራሮች የተለያዩ ፎረሞች አዘጋጅታለች፡፡

ክኔዌንዶ እንግሊዝ ሃገር ከሚገኘው ሱሴክስ ዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፍ ኢኮኖሚክስ ሁለተኛ ዲግሪዋን ያገኘት ስትሆን ታዋቂውን ቼቭኒንግ ስኮላርሺፕ እኤአ በ2012 ተጠቃሚ ሆናለች፡፡

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram