የደም ናሙና ሳይወስድ የደም ስኳርን ለመለካት የሚያስችል የቴክኖሎጂ ውጤት ይፋ ሆነ
የደም ናሙና ሳይወስድ የደም ስኳርን ለመለካት የሚያስችል የቴክኖሎጂ ውጤት ይፋ መሆኑ ተገልጿል።
ቴክኖሎጂው በዋተርሎው የንቨርሲቲ የበጎ ፈቃደኞች ላይ ተግባራዊ ተደረጎ 85 በመቶ ያህል ትክክለኛ መረጃ መስጠቱም ታውቋል።
የስኳር መጠንን ለመለካት ከእጅ ጣት ላይ የደም ናሙና መውሰድ የተለመደና የህመም ስሜት ያለው ሲሆን፥ አዲሱ ቴክኖሎጂ የደም ስኳርን ለመለካት በእየጊዜው የምንሰጠውን የደም ናሙና እንደሚያስቀር ነው የተገለጸው።
በዋተርሎ ዩንቨርሲቲ የምህንድስና የትምህረት ክፍል ፕሮፌሰር የሆኑት ጆርጅ ሻከር ቴክኖሎጂው በሰውነት ውስጥ ያለን ደም ያለ ምንም ንክኪ ወይንም ናሙና የደም የስኳር መጠንን ለመለካት ማስቻሉን ገልጸዋል።
ቴክኖሎጂው ወደ ደም ክፍል የራዲዮ ሞገድ በመላክና በደም ውስጥ ያሉ መረጃዎችን እንደገና በራዲዮ ዌብ መረጃዎችን የሚሰበሰብ መሆኑ ነው የተገለጸው።
በዚህም በራዲዮ ዌብ ቴክኖሎጂው ከደም ውስጥ የሰበሰባቸውን መረጃዎች ወደ ዲጅታል መረጃዎች በመቀየር የደም ስኳር መጠንን ለመለየት እንደሚችል ነው የተገለጸው።
የዚሁ ቴክኖሎጂ ውጤት በሚቀጥሉት 5 ዓመታት እንደ ሰዓት በእጅ በሚታሰር መልኩ እንደሚቀርብም ነው ፕሮፌሰር ሻከር የገለጹት።
መዚሁ ቴክኖሎጂ ግኝት የዋተርሎ ዩንቨርሲቲ፣ የራዳርና የአርቲፍሻል ኢንተለጀነስ ተመራማሪዎች መሳተፋቸውን ዘገባው ያስረዳል።
ምንጭ፦ upi.com
የተተረጎመው፦ በእንቻለው ታደሰ