fbpx
AMHARIC

የኬኒያው ተቃዋሚ ኦዲንጋ በገዥው ፓርቲ ላይ የሚደረገው የጥላቻ ዘመቻ እንዲቆም ደጋፊዎቻቸውን ጠየቁ

የኬንያ ተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ለደጋፊዎቻቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት በገዥው ፓርቲ ጁቪሊስ እና በፕሬዝዳንቱ ኡሁሩ ኬንያታ ላይ ደጋፊዎቻቸው የሚያደርጉትን ማጥላላት እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎች ከአሁን በፊት ገዥው ፓርቲ በሚያካሂደው የንግድ ስራ እና ምርቶቹ ላይ የማጥላላት ዘመቻ እንዲያቆሙ የተቃዋሚው መሪ ጥሪ ያቀረቡት ከፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ጋር ባደረጉት ስምምነት መሰረት ነው፡፡ 
ራይላ ኦዲንጋ ይህን መግለጫ ያስተላለፉት ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ቀን ሜይዴይ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ውስጥ በተከበረበት ወቅት ነው፡፡

ባለፈው መጋቢት ወር ላይ ሁለቱ ባላንጣ መሪዎች አብረው ለመስራት መስማማታቸው የሚታወስ ሲሆን የአሁኑ ንግግራቸው ደግሞ በመሃከላቸው የሚኖረውን ቁርኝት በማጠናከር ለጋራ ልማት እንደሚቆሙ ያላቸውን አንድነት የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡

በተቃዋሚዎች የማጥላላት ዘመቻ የአገሪቱ ትልቁ የቴሌኮም ኩባንያ እና ብሩካሲድ የተባለው አንድ ከፍተኛ የወተት ተዋጽኦ ኩባንያ የጥቃቱ ሰለባ እንደነበሩ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram