fbpx
AMHARIC

የካርበን ጋዝን ለመሰብሰብ የሚያስችል ቴክኖሎጂ የሙከራ ትግበራ ላይ ሊውል ነው

የብሪታኒያው ሊድ ዩንቨርሲቲ ከባዮ ፊውል ሃይል ምንጭ የሚወጣ በካይ ጋዝ ወደ ከባቢ አየር እንዳይገባ ለመቆጣጠር የሚያስችል ቴክኖሎጂ አገልግሎት ላይ ለማዋል አየሰራ መሆኑ ተገለጸ ።

ድራአክስ ሃላፊነቱ የተወሰ ኩባንያ የመጀመሪያውን የአዲሱን ፈጠራ የሙከራ ትግበራ በዚህ ወር በሰሜን ዮርክሺሬ የሃይል ታዳሽ የኤሌክትሪክ ሃይል ፕሮጀከት ጣቢያ አገልግሎት ላይ እንደሚያልም ታውቋል።

ቴክኖሎጂው በፈረንጆቹ 2009 የተገኘ የብሪታኒያው ሊድ ዩንቨርሲቲ ፈጠራ ሲሆን፣ የንግድ ፣ የሃይል ፣ የኢንዱስትሪ ስትራቴጂ ተቋማትን ትኩረት መሳቡ ተገልጿል።

በኦርጋኒክ ኬሚስትሪ ፕሮፌሰር የሆኑትና የዚህ ቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለቤት የሆኑት ችሪስ ራይነር አዲሱ ቴክኖሎጂ ወጭ ቆጣቢ፣ የካርበንን ልቅት በመቆጣጠርና የከባቢ አየር ሙቀትን ለመቀነስ የሚያስችል ትልቅ ስራ ነው ብለዋል።

በቤተ ሙከራ ደረጃ የተሰበሰበው አየርን እንደገና አገልግሎት ላይ ለማዋል በሚቻልበት ሁኔታ ላይም እየተሰራ መሆኑን ችሪስ ራይነር ተናግረዋል።

የሙከራ ትግበራው በስነህይ ወታዊ መንገድ ከሚፈጠር ሃይል ምንጭ የሚወጣን ካርበን ዳይኦክሳይድ የመሰብሰብ ፈጠራ ወደ ማህበረሰቡ ለማሸጋገር ይረዳል ተብሏል።

ቴክኖሎጂው በብሪታኒያ የካርበን ዳይ ኦክሳይድ አየር ወደ ከባቢ አየር እንዳይገባ በማድረግ የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ ያስቻለ የመጀመሪያው ፈጠራ ነው ተብሏል።

አዲሱ ፈጠራ ከበካይ ጋዝ ነፃ የሆነ ሀይል ለማመንጨት ከማስቻሉም በላይ የዓለም አቀፉን የከባቢ አየር ሙቀት ለመቀነስ እንደሚያስችልም ነው ዘገባው የሚያስረዳው ።

 

ምንጭ፦leeds.ac.uk

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram