fbpx
AMHARIC

የካሊፎርኒያ የአለማችን 5ኛ ግዙፍ የኢኮኖሚ ባለቤት ሆነች

የአሜሪካ ግዛት የሆነችው ካሊፎርኒያ እንድ ሃገር ሳትቆጠር ብሪታኒያን በመብለጥ የአለማችን 5ኛ ግዙፍ የኢኮኖሚ ባለቤት ሆነች፡፡

በአጠቃላይ በመታዊ የሀገር ውስጥ ምርት 2.7 ትሪሊዮን ዶላር ያላት ካሊፎርኒያ ኢኮኖሚያዋ ያደገው በግዛቲቱ በሪልስቴትና በፋይናንስ አገልግሎት ዘርፍ መነቃቃት መታየቱን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡ 

‹‹ወርቃማዋ ግዛት›› በሚል ቅጥያ ስም የምትታወቀው ካሊፎርኒያ ከአውሮፓዊያኑ 2016 እስከ 2017 ባለው ጊዜ በአጠቃላይ ዓመታዊ የሀገር ውስጥ ምርቷ በ127 ቢሊዮን ዶላር አድጎ እንደነበር ተነግሯል፡፡

በዚህም ጠንካራ የምርት እድገት አጠቃላይ ዓመታዊ የሀገር ውስጥ ምርቷ 2.7 ትሪሊዮን ዶላር ሊደርስ መቻሉን ተጠቅሷል፡፡

ይህም ሲሆን ግዛቲቱ ብሪታኒያን በመብለጥ የአለማችን 5ኛ ግዙፍ የኢኮኖሚ ባለቤት ለመሆን እንደበቃች ነው የተነገረው፡፡

ብሪታኒያ ከአውሮፓዊያኑ 2016 እስከ 2017 ባለው ጊዜ በውጭ ምንዛሬ ተመን መዋዠቅ ሳቢያ የሀገረ ውስጥ ምርትመጠኑ ቀንሶ እንደነበርም ተወስቷል፡፡

በአሁን ወቅት የአለማችን ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤቶች በቅደም ተከተል አሜሪካ፣ ቻይና፣ ጃፓንና ጀርመን ናቸው፡፡

40 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ያላት ካሊፎርኒያ ደግሞ የአለማችን 5ኛው ግዙፍ ኢኮኖሚ ሆናለች፡፡

ምንጭ፦ ዴይሊ ሜል

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram