fbpx
AMHARIC

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ተካሂደዋል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ የተካሄዱ ሲሆን፥ ጧት 4፡00 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተገናኙት መቐለ ከተማ እና ፋሲል ከተማ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

ሁለተኛው ጨዋታ 9፡00 ሰዓት ላይ የተካሄደ ሲሆን፥ ኤሌክትሪክ ከሀዋሳ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ረቷል፡፡

አዲግራት ላይ ወልዋሎ ደደቢትን ሀዋሳ ላይ ሲዳማ ቡና ድሬዳዋ ከተማን በተመሳሳይ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ረተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ላይ አርባምንጭ ከተማ ከወላይታ ድቻ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

ነገ የሚካሄዱ የ26ኛ ሳምንት ሁለት ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚደረጉ ሲሆን፥ መከላከያ ጅማ አባጅፋርን 10፡00 ሰዓት ላይ ይገጥማል እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና እና አዳማ ከተማ 12፡00 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ፡፡

ፕሪምየር ሊጉን ዛሬ ጧት ከፋሲል ከተማ ጋር አቻ የተለያየው መቐለ ከተማ 43 ነጥብ በመያዝ በመምራት ላይ ይገኛል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወልዲያ ጋር 11፡30 ላይ የሚገናኝ ሲሆን ወልዲያን የሚያሸንፍ ከሆነ የመሪነት ደረጃውን ይረከባል፡፡

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram