fbpx
AMHARIC

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሀገር ውስጥና በውጭ የነበሩት ሲኖዶሶች በአንድ ሲኖዶስ ለመመራት ተስማሙ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሁለቱ ሲኖዶስ የነበረው ልዩነት በዕርቀ ሰላም ወደ አንድነት ተመለሰ።

ባለፉት 27 ዓመት በሁለት ሲኖዶስ ስትመራ የቆየችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርሲቲያን ወደ አንድ ለማምጣት የሰላምና የእርቅ ጉባዔው በዋሸንግተን ደብረ ሀይል ቅዱስ ገብርዔል ቤተክርስቲያን ባለፈው እሁድ የሁለቱም ልኡካን አባቶች በተገኙበት የጋራ ጸሎትና የመክፈቻ መርሐ ግብር ተጀምሯል።

ሲኖዶሶቹ ለሁለት በመከፈላቸው ምክንያት ችግር ላይ የነበሩ የእምነቱን ተከታዮች ወደ አንድነት ለማምጣት በሚቻልበት ሁኔታ ውይይት በማድረግ ወደ አንድነት እንደተመለሱ ታማኝ ምንጮች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

በእስካሁኑ ውይይታቸው በአንድ ሲኖዶስ ለመመራት ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ነው የተነገረው።

በተጨማሪም “የሀገር ቤት ሲኖዶስ” እና “ስደተኛ ሲኖዶስ” የሚባለውን ለማስቀረት ተስማምተዋል።

ይህ የሰላምና የእርቅ ጉባዔ እስከ አርብ ድረስ የሚቆይ እንደሆነና በውይይቱ መጨረሻ መግላጫ እንደሚሰጥ ነው የተገለፁው።

በቅርቡ ወደ አሜሪካ ያቀኑትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አሸማጋይ ኮሚቴ አባላትን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በፅህፈት ቤታቸው ማነጋገራቸው የሚታወስ ነው።

በዚህ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የአስታራቂ ኮሚቴ አባላቱ በእርቅና ሰላም ረገድ አርዓያ መሆን እንዳለባቸው በመጥቀስ፥ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሰላም የሀገር ሰላም እንደሆነ ተናግረዋል።

ቤተ ክርስቲያኗ የጠፋውን ሰላም ወደ ነበርበት እንዲመለስ ለማድረግም ከ2003 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ከዚህ በፊት ማስታወቀቸው ይታወሳል።

በ2010 ዓመተ ምህረት ጥቅምት ወር የቤተ ክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔን ተከትሎ በራሱ ተነሳሽነት ከካህናትና ምእመናን የተወጣጣ የሰላም ኮሚቴ ያቀረበውን የዕርቅ ጥያቄ ተቀብሏል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram