fbpx
AMHARIC

የኡጋንዳ ፓርላማ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ግብር እንዲከፍሉ የሚያስገድድ አወዛጋቢ ውሳኔ አፀደቀ

የኡጋንዳ ፓርላማ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ግብር እንዲከፍሉ የሚያስገድድ አወዛጋቢ ውሳኔ ማሳለፉ ታወቀ።

በዚህም የፌስቡክ፣ዋትስአፕ፣ ቫይበር እና የትዊተቀር ተጠቃሚዎች በቀን ውስጥ 200 የኡጋንዳ ሽልንግ ወይንም 0 ነጥብ 05 ዶላር መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ነው የታወቀው።

በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ማህበራዊ ሚዲያ ያልተረጋገጠ እና መሰረት ቢስ የሆነ መረጃዎች ያሰራጫል በማለት ግብሩ እንዲጣል ግፊት ማድረጋቸው ተነግሯል።

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን ግብር ማስከፈሉ ከሀምሌ 1 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ቢገለፅም በምን አይነይት መልኩ ተፈፃሚ ይሆናል የሚለው ግን እያወዛገበ ነው ተብሏል።

የግብር ክፍያው ከማህበራዊ ሚዲያው በተጨማሪ በሞባይ በሚደረገው የገንዘብ ዝውውር ወቅት ላይም የአንድ በመቶ ግብር የተጣለ ሲሆን፥ የመብት ተማጋቾች ደሃውን የህብረተሰብ ክፍል የሚጎዳ ነው በማለት ቅርታ አቅርበዋል።

የሀገሪቱ የፋይናንስ ሚኒስትር ዴቪድ ባሃቲ ለፓርላማው ባደረጉት ንግግር ይህ የግብር ማስከፈያ እያደገው ለመጣው ሀገራዊ እዳ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በአሁን ወቅት የሀገሪቱ መንግስት አገልግለት እየሰጡ የሚገኙት ሲም ካርዶችን ለመመዝገብ ጥረት እያደረገ ነው ተብሏል።

በሀገሪቱ አገልግሎት እየሰጡ ከሚገኙት 23 ነጥብ 6 ሚሊየን ስልኮች 17 ሚሊየን ስልኮች ብቻ የኢንተርኔት አገልግሎት እንደሚጠቀሙ ተነግሯል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram