fbpx
AMHARIC

የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፈተናዎች – ለጥያቄዎ መልስ (ክፍል አንድ)

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃገሪቱን ለማረጋጋት መጀመሪያ መውሰድ ያለባቸው እርምጃዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማንሳት እንደሆነ ብዙዎች ይመክራሉ።

ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ተዋናዮች፣ ዲፕሎማቶችም ጭምር አዋጁ እንዲነሣ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈተናዎች ላይ የጥያቄዎ መልስ ዝግጅት የጋበዛቸው ሁለት ምሁራን ስለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈላጊነትና አተገባበር ምልስ ሰጥተዋል፤ ሌሎችም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈታኝ ሁኔታዎች ተነስተዋል።

ለአድማጮች ጥያቄዎች መልስ የሰጡት በወታደራዊው አስተዳደር ዘመን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የእርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ ኮሚሽነር፣ ቀደም ሲልም የኤርትራ ክፍለሃገር አስተዳዳሪ የነበሩት የሕግ ምሁሩ ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ፣ እንዲሁም በአኵስም ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስና የዓለምአቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ አቶ ገብረመድኅን መዝገበ ናቸው።

ለክፍል አንድ ዝግጅት የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ። VOA

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram