fbpx
AMHARIC

የአምስቱ የመጨረሻዎቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ B-787 ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች የማኔጅመንቱ ድብቅ ቁማር

ANA (All Nippon Airways) በመባል የሚታወቀው የጃፖኑ አየር መንገድ ከቦይንግ ካዘዛቸው በርካታ ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች ውስጥ ቀድመው ተመርተው የነበሩት B787 ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች በነበራቸው የምርት ጥራት ችግር የዲዛይን ደረጃቸውን ስለማያሞሉ እና በዚሁም ምክንያት አውሮፕላኖቹ ምንም ሳይጭኑ ከባድ በመሆናቸው እና የጭነት መጠናቸው ዝቅተኛ በመሆኑ፣ የነዳጅ ፍጆታቸው ከፍተኛ በመሆኑ እና አጭር ርቀት ብቻ መብረር በመቻላቸው በመሳሰሉ ትክክለኛ ምክንያቶች ከቦይንግ አልወስድም ብሎ ስለተዋቸው ፈላጊ አተው ለበርካታ አመታት ቆመው ነበር።

ከነዚህ ውስጥ 5ቱ አውሮፕላኖች በግል ጥቅም አሳዳጆች እና ሀገር ሻጭ ማኔጅመንት ውሳኔ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ተጥለዋል። በቦይንግ አሰራር መሰረት አዳዲስ አውሮፕላኖችን ለአየር መንገዶች ብቻ እንደሚሸጥ ይታወቃል።

በዚህም መሰረት South America አካባቢ የሚገኝ አውሮፕላን ገዝቶ በማከራየት የሚታወቅ አንድ ካምፖኒ እነዚህን አውሮፕላኖች ከመግዛቱ በፊት በዚህ standard ማንም እንደማይከራየው ስለሚያውቅ እና በቀጥታ ቦይንግ ስለማይሸጥለት በድርድር የኢትዮጵያ አየር መንገድ 90 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ ከቦይንግ እንዲገዛው ካደረገ በሆላ ይሄው ካምፖኒ ገንዘብ ጨምሮ ወደ 120 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ መልሶ በመግዛት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ25 አመታት በላይ አውሮፕላኑ እስኪያረጅ ድረስ ተከራይቶ እንዲያበርለት የሚያስገድድ ውል ይሄን ህሊና ቢስ፣ ኪሱ በስርቆሽ የደለበ ፣ ጥፋቱ ከመጠን ያለፈ ማኔጅመንት በማስፈረም ለትውልድ የሚተርፍ እዳ መጣያ ሆነናል (እውነት ይሄ አየር መንገድ የግሉ ቢሆን ይህን ውሳኔ ይወስን ነበር? ይሄው ዛሬም ተዋረዱ ሲላቸው ከጅምሩ ጀምሮ በፋን ብሌድ ዝገት፣ በሞተር ዘይት መፍሰስ በመሳሰሉ አወዛጋቢ ችግሮች ሲገጥመው በቆየው የተገጠመለት Trent 1000 Rolls Royce ሞተር ችግር ምክንያት ፓርቱ እስኪገኝ ድረስ አራቱ አውሮፕላኖች እዳቸው እየተከፈለ ላልታወቀ ረጅም ጊዜ እንዳይበሩ ተደርገዋል።

የዚህ አውሮፕላን የሊዝ ክፍያ በዶላር በወር 800,000 እስከ 1.25 ሚሊየን USD ድረስ ነው (በዚህች በደሀ ሀገር ላይ ይሄ ዶላር ምን ያህል ቁም ነገር ሊሰራ እንደሚችል ማሰብ ነው)። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሌሎቹ B787 ድሪም ላይነሮች የነዚህ ድውይ አውሮፕላኖች መስመርን ለመሸፈን ሲባል ለጥገና መግባት ከነበረባቸው ሰአት በላይ በዚህ ወንጀለኛ ማኔጅመንት ውሳኔ ሴፍቲን በሚፃረር ሁኔታ እየበረሩ ይገኛሉ።

ለመሆኑ ሀገሪቶ ከምትከፍለው የውጪ እዳ ከ60% በላይ የአየር መንገዱ ብቻ እንደመሆኑ ሰራተኛውን አጠፋህ እያለ በማስፈራራት በማሰር በማባረር የሚታወቅ ማኔጅመንት ከዚህ ወንጀል በሆላ ዝም መባሉ አያጠያይቅም? ወይ መንግስተ ተቦርነኤል!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ COO አቶ መስፍን ቢሮ ለምን ተሰብሮ ተዘረፈ? ማን ሰበረው? ምን ተፈልጎ ነው የተሰበረው? ቢሮው የሴኩሪቲ ሀላፊ ቢሮ ፊት ለፊት እንዲሁም ብዙ ሰራተኛ የሚመላለስበት ዋናው ካፍቴሪያ ፊት ለፊት ሆና ማን ደፋር ሰበረው??

እነዚህን አውሮፕላኖች ጨምሮ Trent 1000 Rolls Royce ሞተር የተገጠመላቸው አውሮፕላኖች ሁሉ ሞተራቸው ላይ ያለው ችግር ያለበት ፖርት እስኪቀየር ድረስ አውሮፕላኖቹ በገናናዎቹ የአየር ደህንነት ተቆጣጣሪዎች እንዳይበሩ መታገዳቸው ይታወቃል።

ከዚህም ጋር በተያያዘ ቀድሞ መፈረም የነበረበት ወረቀት CEO አቶ ተወልደ ቢሮ ሳይፈረም ሲገላበጥ ቆይቶ የሚፈለገው መለዋወጫ በጊዜ ሳይገዛ በመቅረቱ እና ሌሎች አየር መንገዶች ቀድመው ጠራርገው በመውሰዳቸው ፖርቱ መገኘት አልቻለም።

ኪሳራውም በቀን 110,000 ዶላር በላይ ይገመታል ። በዚህም ምክንያት የአውሮፕላኖቹ መቆም የፈጠረው መዘዝ ጎልጉሎ ያወጣው የአውሮፕላኖቹ የሽያጭ እና ሊዝ ሚስጢር ያለ ጥናት ችግራቸው እየታወቀ በ CEO ትእዛዝ በመገዛታቸው በቀጥታ የአየር መንገዱን CEO ተጠያቂ አድርጎቸዋል። ከዚህም ለማምለጥ ይሄን ጉዳይ አቶ መስፍን ላይ ለመለጠፍ ቴክኒካል የሆኑትን ጉዳዮች የአማከረኝ እሱ ነው ለማለት እንዲችሉ ሰውየው ጠንቃቃ ስለሆነና እንዲህ አይነት ጉዳይ ውስጥ እንደሌለበት መረጃ ስለሚኖረው በድንገት ቢሮውን አሰብረው ላፕቶፑን እና ዶክመንቶቹን አዘረፉት። ወይ መንግስተ ተቦርነኤል!

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram