fbpx
AMHARIC

የናይጄሪያ የህዝብ ብዛት 200 ሚሊዮን መድረሱን የሀገሪቱ ስታስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ

እኤአ በ2006 የናይጄሪያ የህዝብ ብዛት 140 ሚሊዮን የነበረ ሲሆን በአስር አመት ጊዜ ውስጥ 60 ሚሊየን በመጨመር ወደ 2 መቶ ሚሊዮን መድረሱን የብሔራዊ ስነህዝብ መረጃ ኃላፊ ኢዚ ዶርማ ለቢቢሲ ተናግረዋል ፡፡

በህዝብ ብዛት ከዓለም ሰባተኛ የሆነችው ናይጀሪያ በ30 ዓመታት ውስጥ ፓኪስታንን ፣ብራዚልን፣ ኢንዶኔዥያን እና አሜሪካን በልጣ ቻይና እና ህንድን ተከትላ ሶስተኛዋ የዓለማችን ባለብዙ ህዝብ ሀገር እንደምትሆን ተገምቷል፡፡

ያልተመጣጠነ የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ብሄራዊ አደጋ እንደሚያስከትል የሚናገሩት የእንግሊዝ የስነህዝብ አጥኚዎች ባሁኑ ሰዓት ናይጀሪያ የህዝብ ብዛቷን ተቆጣጥራ ከኢኮኖሚዋ ጋር ባለመጣጣሟ የሥራ አጦች ቁጥር ሊጨምርባት እንደሚችል ተገምቷል፡፡

ናይጄሪያ በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን ኢትዮጵያ እና ግብጽ ደግሞ ይከተሏታል፡፡

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram