fbpx
AMHARIC

የቻይና ተመራማሪዎች የወባ በሽታ መዲሃኒትን ከእጸዋት እንዳገኙ ገለጹ

የቻይና ተመራማሪዎች እጸዋቶችን በማዳቀል ከእፀዋት የሚገኘውን ‘‘አርተሚሲን’’ የተባለውን የወበ በሽታ መድሃኒት ንጥረ ነገር ምርታማነት በሶስት እጥፍ እንዳሳደጉ ተገለጸ ።

የጥናቱ ዓላማ ‘‘አርተሚሲን’’ የተባለውን መድሃኒት በሰፊው ከእጸዋቶች በማምረት በዓለም አቀፍ ደረጃ የወባ ህሙማን የደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት እንደሆነም በሻንጋይ ጃሁ ቶንግ ዩንቨርሲቲ የጥናቱ ተባባሪ ኬኡዛን ታንግ ተናግረዋል።

የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያመላክተውም በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2016 በ91 ሀገራት 216 ሚሊየን ህዝብ በወባ በሽታ የተጠቃ ሲሆን፥ ከዚም መካከል 445 ሺህ ያህሉ ህይወታቸው እንዳለፈ ይገመታል ተብሏል።

ከዓለም አቀፉ ህዝብ 50 በመቶ ያህሉ የወባ በሽታ ተጠቂ እንደሆነም በዘገባው ተገልጻል።

በታዳጊ ሀገራት በገዳይነቱ ለሚታወቀው የወባ በሽታ ‘‘አርተሚሳ አኑኣ’’ የተባለው ንጥረ ቅመም ፍቱን መድሀኒት እንደሆነ በዮርክ ዩንቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ኢያን ግርሀም ተናግረዋል።

ምርምሩ መድሃኒቱን ከእጸዋቶች በሰፊው በማምረት በተመጣጣኝ ዋጋ ለዓለማቀፉ ማህበረሰብ ለማቅረብ ያስችላል ነው የተባለው።

ቀደም ሲል ከእጸዋቱ በቂ ‘‘አርተሚሲን’’ የተባለ ንጥረ ነገር ይገኝ እንዳልነበረም ‘‘ሞሎኩላር ፕላንት’’ በተባለው ጆርናል ለህትመት በቅቷልም ተብሏል።

የተመራማሪዎች ቡድን በእጸዋቱ ላይ ባደረገው ምርምር ጥራት ያለው ‘‘አርተሚሲን’’ የተባለ ንጥረ ነገር እንደተገኘም ታውቋል።

ጥናቱ ረዘም ያለ ጊዜ የወሰደ ሲሆን፥ ግኚቱ ለገበያ ከመቅረቡ በፊት ተደጋጋሚ ሙከራዎች እንደሚደረጉበትም በዘገባው ተገልጿል።

የጥናቱ ቡድን ‘‘አርተሚሲኒን’’ በተባለው ንጥረ ቅመም የበለጸጉ እፅዋት ዘሮችን ወደ ማዳጋስካር የላኩ ሲሆን፥ እጸዋቱ በአፍሪካ ሀገራት በቀላሉ መራባት እንደሚችሉም ነው የተገለጸው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram