fbpx
AMHARIC

የትግራይ ክልል በአዲስ አበባው የቦንብ ጥቃት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባለፈው ቅዳሜ በሀገሪቱ እየመጡ ላሉ ለውጦች ድጋፍ እና እውቅና መስጠትን ዓላማ ባደረገው ሰልፍ ላይ በደረሰ የቦምብ ጥቃት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ማቋቋሚያ የሚሆን 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

የክልሉ መግስት በጥቃቱ እጅግ ማዘኑን ገልፆ በድጋፍ ሰልፉ የደረሰውን ጥቃት ባወጣው መግለጫ አውግዟል።

በቅርቡ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በመስቀል አደባባይ የቦምብ ፍንዳታ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች መጎብኘታቸው ይታወሳል።

በዚህ መግለጫ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ማንነትን መሰረት አድርገው እየተፈጸሙ ያሉ ጥቃቶችና እንደሚያወግዝም አስታውቋል።

ዜጎችን በማንነት በመለየት ጥቃት መፈፀም የዜጎችን ህገ መንግስታዊ መብትና ነፃነትን የሚፃረሩ እንደሆነ በመግለጫው አመልክቷል።

የኢፌዴሪ መንግስትና ክልሎችም የዜጎች መብትና ነፃነት ሳይሸራረፉ እንዲያስከብሩ ጠይቋል።

ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተፈናቀሉ የክልሉ ተወላጆችን በዘላቂነት ለማቋቋምም የትግራይ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ መወሰኑን የክልሉ የመንግስትና ህዝብ ግኑኝነት ቢሮ አስታውቋል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram