fbpx
AMHARIC

የትግራይ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው

የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 5ኛ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባዔ በመካሄድ ላይ ነው።

የምክር ቤቱ መደበኛ ጉባዔ እስከ ሰኔ 30 እንደሚቆይ ተገልጿል።

ዛሬ በተጀመረው መደበኛ ጉባዔ ላይ የምክር ቤቱን ዓመታዊ ሪፖርት፣ የምክር ቤት፣ የከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የክልሉን ስራ አስፈጻሚ ሪፖርት ቀርቦ በመወያየት ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

እንዲሁም የዋና ኦዲተር እና የመገናኛ ብዙኀን ኤጀንሲ ሪፖርትም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት እንደሚፀድቅ ይጠበቃል።

በተጨማሪም በመደበኛ ጉባዔው የክልሉ መንግስት የ2011 በጀትእንደሚጸድቅ የህዝብ ግንኙነትና የኮንፍረንስ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ታረቀ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል።

የዓሳ ሃብት ረቂቅ አዋጆችን፣ የፍትሃብሄር  ዳኝነት ክፍያ ማስቀረት ላይ ተወያይቶም ያጸድቃል ተብሎም ነው የሚጠበቀው።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram