fbpx
AMHARIC

የተማሪዎችን የፊት ገጽታ በመመልከት ትምህርታቸውን በትኩረት መከታተል አለመከታተላቸውን የሚለየው ካሜራ

አንድ የቻይና ትምህርት ቤት ተማሪዎች ክፍል ውስጥ በትኩረት እየተማሩ መሆን አለመሆኑን የሚቆጣጠር ካሜራ ስራ ላይ አውሏል።

በቻይና ሀንግዡ ቁጥር 11 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተገጠመው ካሜራ የተማሪዎችን የፊት ገፅታ በመቅረፅ ተማሪዎች በትኩረት እየተከታተሉ መሆን አለመሆናቸውን ያሳውቃል ተብሏል።

ዘመናዊ የክፍል ውስጥ ባህሪ መከታተያ ስርዓት በሚል የተጀመረው በቴክኖሎጂ የታገዘ ቁጥጥር በመላ ቻይና ተግባራዊ እንደሚሆንም ነው የተጠቆመው።

ስርዓቱ በትምህርት ቤቱ አንድ ክፍል ውስጥ ብቻ ለሙከራ የተተከለ ሲሆን በበጋ ወራት በሁሉም ክፍሎች እንደሚተከል የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ኒ ኒዩአን ተናግረዋል።

ዘመናዊ የክፍል ውስጥ መቆጣጠሪያ ስርዓቱ መተግበሩን ተከትሎ በክፍሉ ውስጥ የተወሰኑ ተማሪዎች ቀድሞ ከነበራቸው ባህሪ ለውጥ ማሳየታቸውን ገልፀዋል።

አንድ ተማሪ በሰጠው አስተያየትም “ቀድሞ ክፍል ውስጥ ስገባ ትምህርት ያስጠላኛል፤ ሰነፍ ነበርኩ፤ ጠረጴዛ ተደግፌ እተኛለሁ፤ ወይም ደግሞ በመጽሐፍ ከሌሎች ጋር እንደባበድ ነበር” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

ይህ ተማሪ “ካሜራው በክፍላችን ውስጥ ከተተከለ ወዲህ ግን ከፊት ለፊቴ እየቀረፁኝ መሆኑን ስለማውቅ ትምህርቴ ላይ ትኩረት እያደረግኩ ነው” ብሏል።

ካሜራው ከተማሪዎች የፊት ገፅታ ላይ የተለያዩ ስሜቶችን በማንበብ ወደ ኮምፒዩተር የሚልክ ሲሆን፥ ተማሪዎች በሚሰጣቸው ትምህርት ደስተኛ ሆነው እየተከታተሉ መሆን ወይም አለመሆኑን ለመከታተል አመቺ ሆኗል።

ኮምፒውተሩ ከካሜራው ከሚላክለት የተለያዩ ስሜት ገላጭ ምስሎች የደስታ፣ የመከፋት፣ የመረባበሽ፣ የመበሳጨት፣ የመደነቅ እና የመፍራትን ጨምሮ ሰባት ስሜቶችን ይተነትናል።

የስሜት ትንታኔ ከሰራ በኋላ ተማሪዎች በትኩረት እየተማሩ ካልሆነ ወይም ሌላ ሀሳብ ላይ ከሆኑ ወዲያውኑ መፍትሄ እንዲሰጥ ለመምህሩ መልዕክት ይልክለታል ነው የተባለው።

የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አዲሱ የመቆጣጠሪያ ስርዓት የትምህርት መሻሻልን ያመጣል ብለው ቢናገሩም የተማሪዎችን ነፃነት እየተጋፋ ነው የሚሉ ወገኖች ተቃውመውታል።

ምንጭ፦ ቴሌግራፍ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram