fbpx
AMHARIC

የቀድሞዋ የደበብ ኮሪያ መሪ የ24 ዓመት የእስር ቅጣት ተፈረደባቸው

የቀድሞዋ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ፓርክ ገዩን በስልጣን ዘመናቸው በፈጸሟቸው ሙስናና ብልሹ አሰራሮች የ24 ዓመት የእስር ቅጣት ተፈርዶባቸዋል።

ፍርድ ቤቱ በተጨማሪም የ17 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ቅጣት አሳልፎባቸዋል።

የፓርክ የፍርድ ሂደት በሀገሪቱ ቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ለህዝብ የቀረበ ሲሆን፥ በሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናትና የንግድ ሰዎች ዘንድ ቁጣ እንደቀሰቀሰም ተነግሯል።

የፍርድ ሂደቱ ለህዝብ በቀጥታ ቴለቪዥን ሲቀርብ ባለ ጉዳዮዋ ፓርክ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡም ታውቋል።

ፓርክ የተላለፈባቸው ፍርድ ተገቢና ትክክለኛ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

ኪም ሰዩን የተባሉት የሀገሪቱ ዳኛ ፓርክ በርካታ ሀገራዊ ጥፋት ያደረሱ ቢሆንም፤ ምንም አይነት የጸጸት ስሜት አላሳዩም ብለዋል።

በዚህም የተገኘውን መረጃ መሰረት በማድረግ የቀድሞዋን ፕሬዚዳንት ተጠያቂ አድርገናቸዋል ብለዋል።

በሀገሪቱ ቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት የቀረበው የፓርክ የፍርድ ሂደት ከዚህ ቀደም ያልተለመደ መሆኑ ተነግሯል።

የሀገሪቱ ባለስልጣት በበኩላቸው ሂደቱን የህዝብን ፍላጎት ከመጠበቅ አንፃር የቀጥታ ሽፋን መስጠታቸው ተነገረዋል።

ፓርክ ከ16 እስከ 18 በሚደረሱ ከሙስና ጋር በተያያዙ ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆነው መገኘታቸው በዘገባው ተጠቅሷል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram