fbpx
AMHARIC

የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ነገ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ነገ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ተነገረ፡፡

ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ ቆይታቸውም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነትንና ትብብር በሚጠናከርበት ጉዳዮች ላይ ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

እስካሁን ባለን መረጃ ፖል ካጋሜ የሀገሪቱን መሰረተ ልማቶችና የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንደሚጎበኙም ታውቋል፡፡

ይህም ሩዋንዳ በልማቱ መስክ በተለይም በመሰረተ ልማት እና ኢንዱስትሪ ግንባታ ኢትዮጵያ ያካበተችውን ልምድ ለመቅሰም እንደሚያስችላት ተነግሯል፡፡

ሩዋንዳ በኢትዮጵያ ኤምባሲዋን የከፈተችው በአውሮፓዊያኑ 1978 ነበር፡፡

ከአውሮፓዊያኑ 1990 ወዲህ በሩዋንዳ ዘላቂ ሰላምና ደህንነት እንዲረጋገጥ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረትና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር በመሆን ከፍተኛ ሚና ተጫውታለች፡፡

በተለይ አውሮፓዊያኑ 1994 የነበረው የዘርማጥፋት እልቂት እንዲቆም ኢትዮጵያ የራሷን የሰላም አስከባሪ ሀይል በሀገሪቱ በማሰማራት የበኩሏን አስተዋጽኦ አበርክታለች፡፡

ሩዋንዳ በበኩሏል በኢትዮጵያና በኤርትራ ያለውን ውዝግብ በሰላም ለመፍታት የራሷን ጥረት ለማደረግ ተንቀሳቅሳ ነበር፡፡

ጠንካራ የዲፕሎማቲክ ግንኙነት እንዳላቸው የሚነገርላቸው ኢትዮጵያና ሩዋንዳ በበርካታ ዘርፎች ተባብረው ይሰራሉ፡፡

ከእነዚህም ውስጥ በግብርና፣ ጤና፣ አየር ትራንስፖርት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ ትምህርት፣ ንግድና በባህል የልማት መስኮች ላይ ሁለቱ ሀገሮች በትብብር እንደሚሰሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram