fbpx
AMHARIC

የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ በሃዋሳ ይፋዊ የእራት ግብዣ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ጉብኘት በማድረግ ላይ ለሚገኙት የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ በሃዋሳ ይፋዊ የእራት ግብዣ አሰናድተውላቸዋል።

በእራት ዝግጅቱ ላይ የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ከኢትዮጵያ አጠቃላይ የልማት እንቅስቃሴ እና ጥረት አገራቸው የምትማረው ብዙ ነገር እንዳለ ገልፀዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ጋር በሁለትዮሽና የአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ተባብረው ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ጠቅሰው ዶ/ር አብይ ሩዋንዳን እንዲጎበኙ ጋብዘዋል።
የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ላደረጉላቸው ግብⶳ አመስግነዋል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ፕሬዚዳንት ካጋሜ ሩዋንዳን ከእርስ በእርስ ጦርነት ወደልማት የመሩ ፖለቲከኛ ናቸው ብለዋል፤ በአፍሪካ የሰላምና ደህንነት ጉዳይ ላይ ካጋሜ ገንቢ አስተዋጽኦ ያደረጉ መሆናቸውን በመግለፅም የአፍሪካ መስራች አባቶችን የሰላምና የልማት ራዕይ ለማሳካት በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

በሀዋሳ በነበራቸው ጉብኝት በክልሉ እይተሰሩ ባሉ የኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት መደሰታቸውን ገልጸው የክልሉ ህዝብ ላደረገላቸው ደማቅ አቀባበል የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።

በሁለቱ ሀገራት ያለው የወንድማማች ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር እጅ ለእጅ ተያይዘው መጓዝ እንዳለባቸው ጠቅሰው፤ በክልሉ እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተበረከተላቸው ስጦታ አመስግነዋል።

Source:- MOFA

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram