fbpx
AMHARIC

የማሊ የሰላም ስምምነት ተግባራዊ እንዲደረግ ተመድ ጠየቀ

በማሊ ለማካሄድ የታቀደው ምርጫ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ በፈረንጆቹ 2015 በሃገሪቱ ተቀናቃኝ ወገኖች መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተግባራዊ እንዲደረግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥሪ አቅርቧል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዋናው ፀሀፊ ልዩ ተወካይና በማሊ ዘርፈ ብዙ የተቀናጀ የሰላም ማረጋጋት ተልእኮ ኃላፊ ማሃመት ሳለህ አናዲፍ ሃገሪቱ አሁን ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢ ቢሆንም የገቡትን የስምምነት ቃል ተግባራዊ በማድረግ ተፎካካሪ ወገኖች የተቀመጠውን ቀነ ገደብ ማክበር እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የምርጫ ሂደቱንና የሰላም ማስፈኑን እንዲፋጠን ለማድረግ ሁለቱም ጎን ለጎን መከናወን እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

ምርጫው ተአማንነትና ግልጽነትን በተሞላበት መልኩ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ መከናወን እንዳለበት ዋንኛ የፖለቲካ ተዋናዮች አንድ አቋም መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡

ከብዙ ውይይትና ድርድር በኃላ የሰላም ስምምነት ማእቀፉን የማሊ መንግስትና ሁለት ተጣማሪ ታጣቂ ቡድኖች እንደተቀበሉት ተነግሯል፡፡

በመጪው ሃምሌ 22/2010 የመጀመሪያው ዙር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን ለማሄድ የታቀደ ሲሆን ጥቅምትና ህዳር ላይ ደግሞ የህግ አውጪዎችን ምርጫ ለማካሄድ ቀነ ቀጠሮ ተይዟል፡፡

ምንጭ:- ሺንዋ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram