fbpx
AMHARIC

የሚያዚያ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ወደ 13 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ ብሏል

አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ ባለፊው መጋቢት ወር ከነበረበት 15 ነጥብ 2 በመቶ በሚያዚያ ወር ወደ 13 ነጥብ 7 ዝቅ ማለቱን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ።

ኤጀንሲው ለፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ በሚያዚያ ወር በምግብ ዋጋ ላይ ቅናሽ የታየ ሲሆን፥ ምግብ ነክ ባልሆኑ ላይ የተወሰነ የዋጋ ጭማሪ መመዝገቡን አመልክቷል።

በዚህም በሚያዚያ ወር የምግብ ዋጋ ግሽበት 16 ነጥብ 1 በመቶ ሆኖ ሲመዘገብ፥ ምግብ ነክ ባልሆኑት ላይ በላፈው ወር ከነበረው የ10 ነጥብ 0 የዋጋ ግሽበት በሚያዚያ ወር ወደ 10 ነጥብ 8 ከፍ ብሎ ተመዝግቧል።

በሚያዚያ ወር የእህል ምርቶች መረጋጋት ያሳዩ ሲሆን፥ የአትከልትና የፍራፍሬ ዋጋ የተወሰነ የዋጋ ቅናሽ ማሳየቱ ተጠቁሟል።

እንዲሁም የበርበሬ ዋጋ ወደ ቀድሞ መመለስ ባይችልም በሚያዚያ ወር ቅናሽ ማሳየቱን ነው ኤጀንሲው ያስታወቀው።

በሌላ በኩል በሥጋ፣ ቅቤ፣ ወተት፣ አይብና ዕንቁላል ዋጋ ላይ በወሩ የዋጋ ጭማሪ እንደተመዘገበ ነው የተነገረው።

በልብስና መጫሚያ፣ በቤት እንክብካቤ፣ በቤት ዕቃዎችና ማስጌጫዎች፣ በቤት መስሪያ እቃዎች (በተለይ የቤት ክዳን ቆርቆሮ) ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ምግብ ነክ ባልሆኑት ላይ የዋጋ ጭማሪው ከፍ እንዲል ማድረጉን ነው ኤጀንሲው ያስታወቀው።

በኤፍሬም ምትኩ – ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram