fbpx
AMHARIC

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲሰረዙ ወሰነ

ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ያደረገው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲሰረዙ ወሰነ።

ምክር ቤቱ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግምባር (ኦነግ)፣ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) እና ግንቦት ሰባት የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው የሽብርተኝነት ፍረጃ እንዲነሳ ነው የውሳኔ ሀሳቡን ማሳለፉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ልዩ ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲሰረዙ የሚጠይቅ ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ እንዲፀድቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልኳል።

ምክር ቤቱ ያሳለፈው ውሳኔ ሀሳብም የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ በሰለማዊ መንገድ እንዲሳተፉ የሚያበረታታ መሆኑንም ገልፀዋል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram