fbpx
AMHARIC

የመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ዛሬ መደበኛ ጉባዔውን አካሂዷል

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ዛሬ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዷል፡፡

በጉባዔውም የአንድ ዓመት የስራ አፈጻጸም ቀርቦም ውይይት ተካሂዶበታል ተብሏል፡፡

ፋውንዴሽኑ ባለፈው አንድ ዓመት ጽህፈት ቤት የማደራጀት ስራዎችን እና በተለያዩ ጊዜያት በአቶ መለስ ዜናዊ የተጻፉ ስራዎችን የመሰብሰብና የመሰነድ ተግባራት ማከናወኑን ገልጿል።

በተያዘው ዓመትም ባለፈው ከታተሙት በተጨማሪ ሌሎች መጻህፍት በተለያዩ የሃገሪቱ ቋንቋዎች ለህትመት እንደሚበቁ ተነስቷል፡፡

የማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውሳኔዎች በፍላጐት ብቻ ሳይሆን በምርምር መደገፍ አለባቸው የተባለ ሲሆን÷ አዳዲስ ፖለቲካዊ ሃሳቦች እንዲፈልቁም ትኩረት ሰጥቶ መስራት አንደሚገባ ተገልጿል፡፡

በፋውንዴሽኑ ስር ያለው የጉለሌ እጽዋት ማዕከል ግንባታም በዚህ ዓመት እየተፋጠነ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በመድረኩ የመለስ ዜናዊን ስም፣ ስብእና፣ ምስል፣ ስራዎችና መታሰቢያዎች አጠባበቅ እና አጠቃቀምን አስመልክቶ የተዘጋጀውን መመሪያ ውይይት ተደርጎበት ጸድቋል።

የመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን በ2005 ዓመተ ምህረት መመስረቱ ይታወሳል፡፡

ኤፍ ቢ ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram