fbpx
AMHARIC

የሐምሌ ወር የዋጋ ግሽበት 14 በመቶ ሆኖ ተመዘገበ

የሐምሌ ወር ሀገራዊ የዋጋ ግሽበት 14 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ።

ኤጀንሲው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ መሰረት የዋጋ ግሽበቱ ካለፈው ወር ጋር ሲነፃፀር የ 0 ነጥብ 7 በመቶ ቅናሽ ማስመዝገቡን ጠቁሟል።

በሀምሌ ወር የምግብ ዋጋ ግሽበት 16 ነጥብ 7 ሆኖ ሲመዘገብ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት ደግሞ የ10 ነጥብ 9 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል።

ከባለፈው ወር ጋር ሲነፃፀር በእህል፣ አትክልትና ፍራፍሬ እና ቅመማ ቅመም ዋጋ ላይ ጭማሪ የተመዘገበ ቢሆንም በዳቦ፣ ሥጋ፣ ቅቤ፣ ወተት፣ አይብ፣ ዕንቁላል ፣ስኳር፣ ማርና ቼኮሌት ላይ መጠነኛ ቅናሽ ታይቷል።

Inflation.jpg

ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ግሽበት ከፍ እንዲል ያደረጉት፦ በአልባሳትና ጫማ፣ የቤት ማደሻ እና ማስዋቢያ ቁሳቁሶች፣ የሀይል ፍጆታዎች እንዲሁም በሆቴሎች

የሚወሰዱ ምግቦችና መጠጦች ላይ ጭማሪ በመታየቱ ነው ተብሏል።

በዚህ ወር የነበረው የዋጋ ጭማሪ ባለፉት ወራት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር መረጋጋት መሳየቱን ኤጀንሲው አስታውቋል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram