fbpx
AMHARIC

የልብ ቅርፅ ያለው የፕላትኒየም ጌጥ አይኗ ውስጥ ያስተከለችው ወጣት

የህክምና ባለሙዎች 3 በ 4 ሚሊሜትር ስፋት ያለው በልብ ቅርፅ የተዘጋጀ ፕላትኒየም በአንዲት ወጣት አይን ላይ መትከላቸው ተነገረ፡፡

በልጂቷ አይን ላይ ፕላትኒየሙን ለመትከል አምስት ደቂቃ የወሰደ ሲሆን ተከላውን ከህመም ነፃ ለማድረግ የተሰጣት የአይን ማደንዘዣ ከሶስት ቀን በኃላ እንደተወገደላት ቀዶ ጥጋነውን ያከናወኑት ዶክትር ኢሚል ቼያን ተናግረዋል፡፡

አይኗ ላይ የተተከለው ፕላቲንየም በጥንቃቄ የተለሰለሰ፣ የታጠፈ እን እንዲያፀባርቅ ተደረገ በመሆኑ ከሶስት ቀን በኃላ ምንም አይነት የህመም ስሜት እንዳልተሰማት ተነግሯል፡፡

ዶክተሮቹ በወጣቷ አይን ላይ ጌጡን ለመትከል የአይን ማደንዘዣ እንደሰጧት እና በአይኗ ውስጥ ሚገኙ ባክተሪዎች ማስወገዳቸው ታውቋል፡፡

ፕላቲንየሙን በወጣቷ አይን ላይ ለመትከል ከውስጠኛው የአይኗ ክፍል 3 ሚሊ ሜትር ስፋት ቆዳ ማንሳታቸው ተነግሯል፡፡

በወጣቷ አይኗ ውስጥ የተተከለው ጌጥ አለርጂ እንደማይፈጥር በአይን ህክምናው ቆዳ ጥገና ዘርፍ የ20 ዓመት ልምድ ያፈሩት ዶክተሩ ተናግረዋል፡፡

ጌጦቹ በልብ እና በኮኮብ ቀርፅ እንደሚዘጋጁ የተገለፀ ሲሆን ይህንም በአምስት ደቂቃ ውስጥ ማስወገድ እንደሚቻል ተነግሯል፡፡

በአሜሪካ የዚህ አይነት የአይን ቀዶ ጥገና ያከናወኑ ሁለት ወይንም ሶስት ሰዎች ብቻ እንደሚገኙ እና ከ325 ሚሊየን ሰዎች መካከል አንድ ብቻ ቀዶ ጥገናውን ያከናውናሉ ተብሏል፡፡

ምንጭ፡- ሚረር

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram