ዋትሳፕ አዲስ የክፍያ ስርዓት ጀመረ
የንግድ አገልግሎታቸውን በዋትሳፕ አፕሊኬሽን ለሚጠቀሙ ድርጅቶች አዲስ የክፍያ ስርዓት ማስጀመሩን ኩባንያው አስታወቀ፡፡
ይህ አዲስ የገበያ ስርዓት የድርጅቱ ባለቤት የሆነውን ፌስቡክ ተጠቃሚ ያደርገዋል እየተባለ ይገኛል፡፡
ኩባንያው አዲሱ አገልግሎት ድርጅቶች ከደምበኞቻቸው ጋር እንዲገናኙ አዳዲስ መተግበሪያዎችን ስራ ላይ እንደሚያውል ያስታወቀ ሲሆን ከነዚህም አገልግሎቶች መካከል የመረካከቢያ ጊዜ እና የማለፊያ አካባቢዎችን ይገኙበታል፡፡
አዲሱ የክፍያ ስርዓት እንደየሀገሩ እንደሚለያይ ያስታወቀ ሲሆን በአሜሪካ ከዜሮ ነጥብ አምስት እስከ ዘጠኝ ሳንቲም ይደርሳል ተብሏል፡፡
ሆኖም አዲሱ የክፍያ ስርዓት ከመደበኛው የኤስኤምኤስ አገልግሎት እንደሚወደድ ተገልጿል፡፡
አዲሱ የክፍያ ስርዓት ይፋ የሆነው የቀድሞ የዋትሳፕ ተባባሪ መስራች የነበረው የኩባንያው ኃላፊ ጃን ኮውም መልቀቁ ከተሰማ ከሦስት ወራት በኃላ ነው ተብሏል፡፡
የፌስቡክ ኩባንያ ከአራት ዓመታት በፊት ነበር ዋትሳፕን በ19 ቢሊየን ዶላር የገዛው፡፡
ምንጭ፦ቢቢሲ
በአብርሃም ፈቀደ
Share your thoughts on this post