fbpx
AMHARIC

ኮንደሚኒየም ቤት የተገኘው ጅብ በነዋሪው ውክቢያ ራሱን ከፎቅ ወረወረ

መጋቢት 16 ቀን 2010 ዓ.ም በቦሌ አራብሳ ኮንዶሚኒየም አራተኛ ፎቅ ከንጋቱ 1 ሰአት የተገኘው ጅብ በነዋሪው ውክቢያ ራሱን ከፎቅ ወርውረ።
ከፎቅ በመውደቁ ብቻ ሳይሆን በነዋሪው ከባድ ድብደባም ህይወቱ ወዲያው አላለፈም ነበር።

ሆኖም በስተመጨረሻ የጅቡ ልዩ ልዩ አካል ለመድሀኒትነት ያገለግላል ያሉ ሁለት ሰዎች ጅቡን ተሸክመው በመውሰድ ባርከው ቆዳውን ገፈውታል።
ስጋውንም እየበለቱ ለያይተውታል። በርካቶችም የጅቡን ቁራጭ ስጋ ለመውሰድ በገፋፊዎቹ ዙሪያ ከበው ሲጠብቁ ታይተዋል።

አንዳንዶች የጅብ ስጋን በቋንጣ መልክ በር ላይ ቋጥሮ ማንጠልጠል እርኩስ መንፈስን ያባርራል የሚል ባህላዊ እምነት እንዳላቸው መረዳት ችያለሁ።
ምጥ የጠናባት ሴትንም በቀላሉ እንድትገላገል ለማድረግ የጅብ ቋንጣው ያገለግላል የሚል የፀና ኋላቀር አስተሳሰብ መኖሩንም በእለቱ በቦታው በነበረኝ ቆይታ መረዳት ችያለሁ።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram