fbpx
AMHARIC

ኮሎምቢያ ኔቶን ልትቀላቀል ነው

የደቡብ አሜሪካዋ ኮሎምቢያ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት ኔቶን ልትቀላቀል መሆኑን አስታወቀች፡፡

ይህንን ያሉት የኮሎምቢያው ፕሬዚዳንት ማኑኤል ሳንቶስ ሲሆኑ፥ በሚቀጥለው ሳምንት ሀገራቸው ድርጅቱን በይፋ ትቀላቀላለች ብለዋል፡፡

አንድ የደቡብ አሜሪካ ሀገር ኔቶን ስትቀላቀል የመጀመሪያው መሆኑ ተገልጿል፡፡

የዛሬ ዓመት ግንቦት ወር ላይ 29ኙ የድርጅቱ አባል ሀገራት ስምምነት መፈጸማቸው ይታወሳል፡፡

ፕሬዚዳንት ሳንቶስ አብዛኛዎቹ ችግሮች ዓለምአቀፋዊ ይዘት እንዳላቸው አንስተው ለዚህም ከሀገራት ጋር ግንኙነት መፍጠር ችግሮቹን ለመቅረፍ መፍትሔ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ሀገራቸው ከዚህ ስምምነት ላይ መድረሷ እንደሚጠቅማት ገልጸዋል፡፡

ኮሎምቢያ በዓለም አቀፍ የደህንነት ጉዳይ ላይ፣ በሳይበር፣ በባህር ደህንነት እንዲሁም በሽብር እና ሌሎች ወንጀሎችን በጋራ ለመስራት መስማማቷን ኔቶ አስታውቋል፡፡

 

 

ምንጭ፥ሮይተርስ
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram