እንግሊዝ በእሳት እየተጫወተች ነው – ሩሲያ
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሩሲያ አምባሳደር ቫስኒ ኒቤንዚያ ለጸጥታው ምክር ቤት ባቀረቡት የሁለቱ ሀገራት የጸብ ምንጭ ሪፖርት ፤እንግሊዝ የሩሲያን ተቀባይነት ለማጣጣልና ዋጋ ለማሳጣት ሆን ብላ የሰርጂ መመረዝን እንደ አጀንዳ በመዘርጋት በእሳት እየተጫወተች ነው ሲሉ ማስጠንቀቂያ አዘል ንግግር አድርገዋል፡፡
የቀድሞው የሩሲያ ሰላይ ሰርጂ ክስ በሀሰተኛ መረጃ የተቀነባበረ ክስ ነው፡፡ሩሲያም የተባለውን ክስ አልፈጸመችም ፡፡
እንግሊዝ ሆን ብላ የሩሲያን ሚና ለማሳጣት ያዘጋጀችው ሀሰተኛ መረጃ ነው ብላለች፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው አምባሳደሩ መሰረተ ቢስ ክስ በመሆኑም ሩሲያ አትቀበለውም ብለዋል፡፡
Share your thoughts on this post