fbpx
AMHARIC

ኢትዮጵያ ከእስር የፈታችው ካናዳዊ ሀገሩ መግባቱ ተዘገበ

ኢትዮጵያ ከእስር የፈታችው ካናዳዊ ሀገሩ መግባቱ ተዘገበ፡፡

ትውልደ ኢትዮጵያዊውና በ 2009 በሽብር ወንጀል የተከሰሰው በሽር ማክታል ካናዳዊ ዜግነት ያለው ሲሆን የእድሜ ይፍታህ እስራት ተፈርዶበት በኢትዮጵያ እስር ቤት ቆይቷል፡፡

የካናዳ ባለስልጣናትና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችም የግለሰቡ እስራት ፍትሀዊ አይደለም በሚል ኢትዮጵያ እንድትለቀው ሲጠይቁ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

በኬንያ በኩል ተሰዶ ካናዳ ለመግባትና ዜግነት ለማግኘት የበቃው በሽር አያቱ የኢትዮጵያ መንግስትን በጦር የሚታገለው የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር አባል የነበሩ ሲሆን እርሱም የተያዘው ከኦኤንኤልኤፍ ጋር ግንኙነት አለው በሚል በሽብር ተወንጅሎ መሆኑን የካናዳ የወሬ ምንጮች አስታውሰዋል፡፡

ምንጭ፡- https://www.thestar.com/

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram