fbpx
AMHARIC

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ በሩሲያው የአለም ዋንጫ በዳኝነት ተመረጡ

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ በሩሲያው የአለም ዋንጫ ጨዋታዎችን በዳኝነት እንዲመሩ ከተመረጡ ዳኞች መካከል አንደኛው ሆነዋል።

አለም አቀፉ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) በዓለም ዋንጫው ላይ ጨዋታዎችን፥ በአርቢትርነት የሚመሩ 36 የመሃል እና 63 ረዳት ዳኞችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማም በሩሲያው የአለም ዋንጫ ከተመረጡት ዳኞች መካከል አንደኛው ሆነው ተመርጠዋል።

ባምላክ ተሰማን ጨምሮ ከአፍሪካ ስድስት ዳኞች ለውድድሩ ተመርጠዋል።

ጋሳማ ከጋምቢያ፣ ጋሃድ ግሪሻ ከግብጽ፣ ሲኪዛዊ ከዛምቢያ፣ ዴዴሆ ከሴኔጋል እንዲሁም አብዲ ሸሪፍ ከአልጀሪያ ከኢትዮጵያዊው ባምላክ ተሰማ ጋር ለአለም ዋንጫው የተመረጡ ዳኞች ናቸው።

ውድድሩን ለመምራት የሚሄዱት ሁሉም ዳኞች ወደ ውድድሩ ከማምራታቸው በፊት ስልጠና ይሰጣቸዋል ተብሏል።

ኢንተርናሽናል አርቢትር ባምላክ ተሰማ የአፍሪካ ዋንጫ፣ የአፍሪካ የክለቦች ውድድር እና የማጣሪያ ጨዋታዎችን በዳኝነት መርተዋል።

ከዚህም ባለፈ በህንድ በተካሄደው የዓለም ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ላይ ተሳታፊም ነበሩ።

በዘንድሮው የአለም ዋንጫ ከተካተቱ 99 መዳኞች መካከል አንድም ብሪታኒያዊ አርቢትር አለተመረጠም ነው የተባለው።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram