fbpx
AMHARIC

አፕል ኩባንያ የፌስቡክ አገልግሎትን ሊያቋርጥ ነው ተባለ

አፕል ኩባንያ የፌስቡክ አገልግሎትን ሊያቋርጥ መሆኑ ተገልጿል።

አፕል ኩባንያ የፌስቡክ ኩባንያ ወደ ፊት አገልግሎት ላይ ሊያውላቸው በሆኑት ‘‘አይኦስ’’ እና ‘‘ኤምኤሲ’’ በተባሉት  ሶፍትዌሮች  አሰራር ምክንያት የፌስቡክ አገልግሎትን ሊቋርጥ መሆኑን ገልጿል።

እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ደንበኞች አገልግሎት ላይ የሚያውሏቸውን የኤክትሮኒክስ መሳሪያዎችንና የሚጫኑ መረጃዎችን የሚሰጡ ናቸው ከሚል ጉዳይ ጋር በተያያዘ ኩባንያው የፌስቡክ አገልግሎትን ሊያቋርጥ መሆኑን ገልጿል።

የፌስቡክ አዲሶቹ ቴክኖሎጂዎች የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ዝርዝር መረጃዎች በመስጠት ለመረጃ ተቋማት አደጋ መሆናቸውም ነው የተገለጸው።

ለዚህም አፕል ኩባንያ ስለበይነ መረብ መጠቀሚ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያውች ውስን መርጃ የሚሰጥ ድረ ገጽ ማልማቱ ታውቋል።

የአፕል ኩባንያ ዋና ስራ አስኪያጅ ቲም ኮክ ቀደም ሲል ይህ አሰራር የደንበኞች ነፃነት መብትን የጣሰ ሲሆን፥ የኩባንያው ዋና ስራ አስኪያጅ ግን ይህን ጉዳይ በተደጋጋሚ ያስተባብላሉ ሲሉ መግለፃቸን ዘገባው አስታውሷል።

የአፕል ኩባንያ የፌስቡክ አገለግሎትን ሊቋርጥ መሆኑን የኩባንያው የሶፍትዌር ልማት መሪ የሆኑት ካራኢጅ ፈደሪግሂ በኩባንያው ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስብሰባ ላይ መናገራቸው የተገለጸ ሲሆን፥ በዚህም በሁለቱ ኩባንያዎች መካከል ውጥረት መንገሱን ነው ዘገባው የሚያስረዳው።

ኩባንያው የፌስቡክ አገልግሎት ከማቋረጡ በፊትም ለደንበኞቹ አማራጭ በመስጠትና መረጃዎቻቸው ላይ ክትትል የሚደረግባቸው ከሆነ የሚያስጠነቅቅ መሆኑም ገልጿል ተብሏል።

 

 

ምንጭ፦ bbc.com

የተተረጎመው፦ በእንቻለው ታደሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram