fbpx
AMHARIC

አፕል አካል ጉዳተኛነትን የሚገልጽ የስሜት መግለጫ ምስሎችን ሊያቀርብ ነው

የቴክኖሎጂ ተቋሙ አፕል (Apple) አካል ጉዳተኞችን በተሸለ መልኩ የሚወክል ስሜትን መግለጫ ምስል (emojis) ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑን ገልጧል፡፡

አፕል ሊተገብራቸው ካሰበው የአዳዲስ ኢሞጂዎች ፕሮፖዛል መካከል ለመስማት ለጆሮ ድጋፍ ማድረጊያ መሳሪያ ፣ ሰው በዊልቸር ላይ ሆኖ፣ ሰው ሰራሽ እጅ እግር ፣ ድጋፍ ሰጪ ውሻ እና በከዘራ የሚንቀሳቀስ ስው ይገኙበታል፡፡

አዳዲሶች ኢሞጂዎች ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩ በ 4 ክፍሎች የተቀመጡ አማራጮች መቅረባቸውን የገለጸው አፕል ለአይነ ስውር እና ለዝቅተኛ እይታ ፣ መስማት የተሳነው እና ለመስማት ለሚቸገሩ ፣ ሰውነታቸውን ማንቀሳቀስ የማይችሉ እና ስውር የአካል ጉዳቶች በሚል መከፋፈሉን አሳውቋል፡፡

የአፕል ኩባንያ ያቀረበው ፕሮፖዛልም አዳዲስ 13 አዳዲስ ስሜት መግለጭ ምስሎችን እንደሚያካትት ተነግሯል፡፡

ምንጭ፡- ሲኤንኤን

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram