fbpx
AMHARIC

አይነስውራን ተሳፋሪዎች መልከዓምድርን መረዳት የሚያስችላቸው ግኝት ይፋ ሆነ

ፎርድ የመኪና አምራች ኩባንያ አይነስውራን ተሳፋዎች በሚጓዙበት አካባቢ ያለውን መልካዓምድር ምን እንደሚመስል መረዳት የሚያስችላቸው ግኝት ይፋ ሆኗል፡፡

ግኝቱ በስማርት መኪኖች መስታወት ላይ የሚገጠም ሲሆን፥ ጥራት ያላቸው ፎቶዎችን በማንሳት ነው ለሚፈለገው አላማ የሚያውለው ተብሏል፡፡

ተሳፋሪዎቹ ታዲያ መስታወቱን በመዳሰስ ብቻ በተለያዩ ሁኔታዎች የሚመጡላቸውን ምስሎች መረዳት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

በሀገሪቱ የሚገኘው የአይነስውራን ተቋም በሙሉ ልቡ የፎርድ ሐሳብን እንደሚደግፍ ተናግሯል፡፡

ከዚህ ግኝት ጎን ለጎን ሰው ሰራሽ የማሰብ አቅም ባላቸው መሳሪያዎች በመታገዝ አይነስውራን አካባቢያቸው ምን እንደሚመስል በድምጽ የታገዘ አገልግሎት ይፋ እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡

የፎርድ ቃልአቀባይ የሰዎችን ህይወት ከዚህ ቀደም ከነበረው የተሻለ የማድረግ ሐሳብ እንዳላቸውና ይህ ሁኔታ ታዲያ አይነስውራን የመኪና ተጓዦችን ለመርዳት መልካም አጋጣሚ እንደሆነላቸው ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፦ቢቢሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram