fbpx
AMHARIC

አውሮፕላኑ በአንድ ሰው የንጽህና ጉድለት ምክንያት ተጓዦች ራሳቸውን በመሳታቸው በአስቸኳይ እንዲያርፍ ተደረገ

ከሆላንድ በመነሳት መዳረሻውን ወደ ስፔን ደሴት ለማቅናት ያለመው አውሮፕላን በአንድ ሰው የንጽህና ጉድለት ምክንያት ተጓዦች ራሳቸውን በመሳታቸው በአስቸኳይ እንዲያርፍ መደረጉ ተሰማ፡፡

በግለሰቡ ምክንያት በርካታ ተጓዦች ራሳቸውን በመሳታቸው እንዲሁም በማስታወካቸው ነው አውሮፕላኑ ፖርቹጋል ላይ በድንገት ሊያርፍ የበቃው፡፡

ተጓዦች እንዳሉት ከሆነ ከግለሰቡ የሚወጣው ሽታ ፍጹም መቋቋም እንዳቃታቸው ገልጸዋል፡፡

አንድ ፔቲ ቫን የምትባል ቤልጄማዊት ስለለግለሰቡ አስተያየቷን ስትሰጥ ለበርካታ ወራት ውሃ ነክቶት የሚያውቅ አይመስለኝም ብላለች፡፡

አውሮፕላኑ እስከሚያርፍ ድረስም ሰራተኞች በመጸዳጃ ቤት ውስጥ እንዳቆዩት ተገልጿል፡፡

ቦይንግ 737 አውሮፕላን በድንገት ካረፈ በኃላ ግለሰቡ በህክምና ባለሙያዎች ወደ አውቶብስ እንዲገባ ተደርጓል፡፡

ኃላፊዎች በመግለጫቸው ቦይንግ 737 ሊያርፍ የበቃው በህክምና ምክንያት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ሆኖም ግለሰቡ በምን ምክንያት እንደዚህ ለመሆን እንበደበቃ የታወቀ ነገር የለም ተብሏል፡፡

1527800197034.jpg

 

ምንጭ፦ ፎክስኒውስ

በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram