አንድ ጊዜ ተዘርተው ለ10 እና 20 አመታት በውሀ ብቻ ምርት የሚሰጡ የጤፍ እና ማሽላ ዝርያዎች በምርምር ተገኙ
የሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር አንድ ጊዜ ተዘርተው ለ10 እና 20 አመታት በውሀ ብቻ ምርት መስጠት የሚችሉ የጤፍ እና ማሽላ ዝርያዎች በምርምር መገኘታቸውን አስታወቀ።
የተገኘው የጤፍ ዝርያ አንድ ጊዜ ከተዘራ በኋላ ለ10 አመት የማይሞት እና በየሶስት ወሩ ውሀ ብቻ ካገኘ ምርት መስጠት የሚችል ነው ተብሏል።
የማሽላው ዘርያ ደግሞ አንድ ጊዜ ተዘርቶ ለ20 አመት ድጋሚ መዝራት ሳያስፈልግ በየሶስት ወሩ ምርት መስጠት ይችላል ነው የተባለው።
አሁን ላይም ዝርያዎቹን ለሃገሪቱ ገበሬዎች ለማከፋፈል የዘር ብዜት ስራ እየተሰራ ሲሆን፥ ዝርያዎቹ በ2011 የምርት ዘመን ለገበሬው የሚከፋፈሉ ይሆናል።
በኢትዮጵያዊ ተመራማሪ የተገኙት እነዚህ ዝርያዎች የኢትዮጵያን የሰብል ልማት ታሪክ መቀየር እንደሚችሉ ታምኖባቸዋል።
በቤተልሄም ጥጋቡ – ኤፍ ቢ ሲ
Share your thoughts on this post