fbpx
AMHARIC

አብርሀም መብራቱ ቀጣዩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አድርጎ ቀጥሯል።

ፌዴሬሽኑ ባሳለፍነው ሳምንት አምስት እጩ አሰልጣኞችን አወዳድሮ አብርሀም መብራቱን አሰልጣኝ ለማድረግ መወሰኑ የሚታወስ ሲሆን ከአሰልጣኙ ጋር ባደረገው ድርድርም በወርሀዊ ደሞዝ እና ሌሎች የኮንትራት ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ደርሷል።

በዚህም መሰረት ወርሀዊ 4500 ዶላር (126,000 ብር) የአሰልጣኙ ደሞዝ ሲሆን የሁለት ዓመት ኮንትራት ተሰጥቷቸዋል። ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችም የውሉ አካል እንደሆኑም ታውቋል።

የቀድሞው የወንጂ ስኳር እና ጉምሩክ አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ የመንን በታሪኳ ለመጀመርያ ጊዜ ለ2019 የኤሺያ ዋንጫ ማሳለፋቸው ይታወቃል።

ምንጭ፣ ሶከር ኢትዮጵያ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram