fbpx
AMHARIC

አሜሪካ እና እንግሊዝ የሳይበር ጥቃት እየፈጸመች ነው ሲሉ ሩሲያ ላይ ክስ አሰምተዋል

የዋሽንግተን እና የለንዶን መቀመጫቸውን ያደረጉ መንግስታት የሩሲያን መንግስት አጥፊ ሶፍትዌሮችን በማስፋፋት በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢንተርኔት መሳሪያዎች ላይ ያነጣጠረ የሳይበር ጥቃትን እየፈጸመች ነው ሲሉ ከሰዋል፡፡
ይህን የሩሲያ ተግባርንም የኢኮኖሚ እና የፖሊቲካ ስለላ ተግባር እንዲያግዛት አጥፊ ሶፍትዌሮች በማስፋፋት ተንቀሳቅሳለች በሚል እየከሰሱ ነው፡፡
ሩሲያ በኢንተርኔት ራውተሮች እና ሌሎች ከኢንተርኔት ጋር ንክኪ ባላቸው መሳሪያዎች ላይ በህገወጥ መንገድ አጥፊ ሶፍትዌሮችን በማሰራጨት ለምትፈጽመው የሳይበር ጥቃት መደላድልን እየፈጠረች ነው ብለዋል፡፡
በጥቃቱ የመንግስት እና የግል ተቋማት ፣ ወሳኝ የሚባሉ መሰረተ ልማቶች እና የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች ይገኙበታል ሲሉ የአሜሪካው የሆምላንድ ሴኪዩሪቲ ፣ የፌደራል የወንጀል ምርመራ ቢሮ (FBI) እና የእንግሊዙ የሳይበር ደህንነት ማእከል ባወጡት የጋራ መግለጫ አሳውቀዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓትም ኢላማ የሆኑ ተቋማት እና ድርጅቶች አሜሪካ እና ሌሎች አጋር አካላት ባደረጉት ጠንካራ የጋራ ስራ መለየታቸውን መግለጫው ተጠቅሷል፡፡
ምንጭ ፡ አሶሼትድ ፕረስ

 

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram