አማዞን የሰዎችን ማንነት በፊት ብቻ መለየት የሚያስችለውን መሳሪያ ለገበያ እንዳያቀርብ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች አሳሰቡ
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የሰዎችን ማንነት በፊት ብቻ መለየት የሚያስችለው መሳሪያ አማዞን ለመንግስት እና ሌሎች መሳሪያን ለሚፈልጉ አካላት ማቅረብ እንደሌለበት አሳሰቡ።
ተሟጋቾቹ ይህ መሳሪያ በስደተኞች እና በቆዳ ቀለም ምክንያት ሰዎች ተፅዕኖ እንደሚደርስባቸው የሚያደርግ በመሆኑ ተግባራዊ መሆን የለበትም ብለዋል።
ከ40 በላይ የሚሆኑት የመብት ተሟጋቾች ለአማዞን የኦንላይን ገበያ ስፍራ ባለቤት ለሆኑት ጆፍ ቤዞስ በላኩት ደብዳቤ ይህ መሳሪያ ሰዎች አላግባብ ጥቃት እንዲደርስባቸው እና መንግስት ተገቢ ያልሆነ ክትትል ስርዓት እንዲዘረጋ ያደደርጋል ብለዋል።
አማዞን በበኩሉ መሳሪያው ወንጀል የፈፀሙ ለማወቅ፣ ዝነኞችን ለመለየት እና የህብረተሰቡን ደህነት ለመጠበቅ እንደሚውል ነው በፈረንጆቹ 2016 ይፋ አድርጓል።
ከበርካታ ሚሊየን ሰዎች ስብስብ መካከል መሳሪያው የተለያ ፍላጎት ያላቸውን ሰዎቸ በቅፅበት በመለየት ወንጀል ለመከላከል እንደሚያስችል ነው አማዞን ያስታወቀው።
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾቹ ለጆፍ ቦዘስ በላኩት ደብዳቤ ይህ ሁኔታ ሰዎች በጎዳኖች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ነፃነት የሚገድብ እንደሆነ ገልፀዋል።
መሳሪያውን የሚጠቀሙ ሰዎች የህግ ድጋፍ ያላቸው እና በአግባቡ ለመጠቀም ሀላፊነት ሊወስዱ የሚችሉ መሆናቸው ተረጋግጦ የሚሰጥ ነው ተብሏል።
ከአማዞን በተጨማሪ ጎግል እና ማይክሮሶፍት ይህን መሳሪያ እንደሚያቀርቡ ተነግሯል።
ምንጭ:- ሮውይተርስ