fbpx
AMHARIC

ተመድ ሜጀር ጄኔራል ገብረ አድሃና ወልደእዝጉን የአቢዬ ሰላም አስከባሪ ኃይል አዛዥ አድርጎ ሾመ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ሜጀር ጄኔራል ገብረአድሃና ወልደእዝጉን የአቢዬ ግዛት ሰላም አስከባሪ ኃይል አዛዥ አድርጎ መሾሙን አስታወቀ።

የተመባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬስ እንደገለጹት ሜጀር ጄኔራል ገብረአድሃና ወልደእዝጉ ተመድ በግዛቱ ያሰፈረው የሰላም አስከባሪ ኃይል አዛዥ ሆነው ተሹመዋል።

ሜጀር ጄኔራል ገብረአድሃና የአገልግሎት ጊዜያቸውን ሚያዚያ 15 ቀን 2010 ዓ.ም የሚያጠናቅቁትን ሜጀር ጄኔራል ተስፋይ ግደይ ኃይለሚካኤልን እንደሚተኩ ተገልጿል።

የአገልግሎት ጊዜያቸውን ያጠናቀቁት ሜጀር ጄኔራል ተስፋይ ግደይ ሀይለሚካኤል የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃትና በውጤታማ በማጠናቀቃቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምስጋናውንና አድናቆቱን አቅርቧል።

ሜጀር ጄኔራል ገብረ አድሃና ወልደእዝጉ በኢትዮጵያ ወታደራዊ ሃይል የ38 ዓመት ልምድ ያላቸውን ሲሆን፤ ከጎረቤት አገሮች ጋር በመሆን የደህንነትና የድንበር ጉዳዮች ለማስተባበር ወደ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳና በአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ተልዕኮ በተደጋጋሚ ጊዜ አቅንተዋል።

በተጨማሪም በዓለም አቀፍና አህጉራዊ የሰላም ማስከበር ተግባራት በወታደራዊ ሃይል ዝግጅት፣ የወታደራዊ ኃይል እቅድና ስምሪት ላይ ተሳትፎ አላቸው ብሏል።

በ1956 ዓ.ም የተወለዱት ሜጀር ጄኔራል ገብረ አድሃና በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በተለያዩ የስልጣን እርከኖች አገልገለዋል። በአሁኑ ወቅትም በመከላከያ ሚኒስቴር በመስራት ላይ ይገኛሉ።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram