በፊፋ ወርሃዊ የአግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ 8 ደረጃዎችን በማሽቆልቆል በ145ኛ ላይ ተቀምጣለች
በፊፋ ወርሃዊ የእግር ኳስ ደረጃ ሰንጠረዥ ኢትዮጵያ ከባለፈው ወር ስምንት ደረጃዎችን በማሽቆልቆል በ145ኛ ደረጃ ላይ ተቀጣለች፡፡
ከአፍሪካ ደግሞ በ40ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
ለዚህ ደረጃዋ ማሽቆልቆልም የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን ለረጅም ጊዜያት የወዳጅነትም ሆነ ሌላ አለም አቀፍ ግጥሚያ ባለማድረጉ ነው ተብሏል፡፡
ከአፍሪካ ቱኒዚያ ቀዳሚውን ስፍራ ስትይዝ ሴኔጋል፤ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፤ ሞሮኮ፤ ግብጽ፤ ናይጄሪያ፤ ካሜሩን፤ ጋና፤ ቡርኪና ፋሶና ኬፕቬርዴ ከ2ኛ እስከ 10 ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ጀርመን አሁንም ቀዳሚውን ስፍራ እንደያዘች ሲሆን ብራዚል፤ ቤልጂየም፤ ፖርቹጋል፤ አርጀንቲና ስዊዘርላንድ፤ ፈረንሳይ፤ ስፔይን፤ ቺሊና ፖላንድ ደግሞ ከ2ኛ እስከ 10 ያለውን ደረጃ ይዛለች፡፡
ምንጭ፡- ፊፋ
Share your thoughts on this post