fbpx
AMHARIC

በጎንደር ህብረተሰቡ ላነሳቸው ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ምላሽ ሰጥተዋል

– የወልቃይትን ጉዳይ በተመለከተ በህግ አግባብ ሊፈታ እንደሚችል ህዝቡ ማመን አለበት ፡፡ ህገ መንግስቱ ይህን ጉዳይ ሊፈታ ይችላል፡፡ በቀጣይም ከወልቃይት ኮሚቴዎች ጋር ውይይት አደርጋለሁ ብለዋል፤ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ በመወያየት ያሉ ጥያቄዎች መመለስ እንችላለን፡፡ ዋናው ነገር በዚህ ሂደት ውስጥ ሀይል የተቀላቀለበት እና ወደ ቁርሾ በሚያስገባ መንገድ መሆን እንደሌለበት ህዝቡ ሊያውቅ ይገባል ብለዋል፡፡

– የሱዳን ድንበር ጋር በተያያዘ ለተነሳው መፍትሄ መሰጠት አለበት ብዬ አምናለሁ፡፡ ድንበር ላይ ያሉ ሁለቱም ወታደሮች እንዲሸሹ እና በአካባቢው ያሉ የሁለቱም ወገን ሰዎች በሰላም እንዲቀሳቀሱ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ነገ ስራዬን እጀምራለሁ፡፡ ነገ በባህር ዳር ለጣና ፎረም ጉባኤ ከሚመጡት የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ጋር በተናጥል ውይይት አደርጋለሁ ብለዋል፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ

– ሌሎች የተነሱ ጥያቄ እና አስተያየቶችን በተመለከተ በአንድ ቀን ጀምበር መመለስ አይቻልም፡፡ በሂደት ላይ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመመለስ እንዲያስችለን ስራዎችን ጀምረናል፡፡ ይሄነው ብዬ ቃል መግባት አልፈልግም፡፡ በተግባር ማሳየቱ ይሻላል፡፡ በቀጣይ በግብርና ፤በኢንዱስትሪ፤በገቢእና በፍትህ ላይ መንግስት የትኩረት ነጥቦች ለይቶ መልስ ለመስጠት ይሰራል፡፡

ይርጋለም አስማማው
ከጎንደር

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram