fbpx
AMHARIC

በየቀኑ መፆም የሰውነት ክብደትንና የደም ግፊትን ለመቀነስ ያስችላል- ጥናት

በየቀኑ መፆም ያልተፈለገ የሰውነት ክብደትንና የደም ግፊትን ለመቀነስ እንደሚያስችል የችካጎ ዩንቨርሲቲ ተመራማሪዎች ገለጹ።

ተመራማሪዎቹ በአማካይ እድሚያቸው 45 ዓመት፣ የቦዲ ማክስ ኢንዴክስ ራሽዮአቸው 35 በሆነ 23 የበጎ ፈቃደኞች ላይ በካሄዱት ጥናት ያልተፈለገ የሰውነት ክብደትንና የደም ግፍት ለመቀነስ መቻሉን አመላከተዋል።

ተጠኚዎቹ በ24 ሰዓት ውስጥ ለ8 ሰዓት የሚፈልጉትን ምግብ መጠንና አይነት እንዲመገቡና በቀሪዎቹ 16 ሰዓታት ውሀ ወይንም ሃይል ሰጪ ያልሆኑ መጠጦችን ብቻ እየጠጡ እንዲቆዩ ተደርጓል።

በዚህ መልኩ በተጠኚዎቹ ላይ ለ12 ሳምንታት ያህል ተመራማሪዎቹ ባደረጉት ክትትል የደም ግፊታቸውና የሰውነት ክብደታቸው እስከ 3 በመቶ መቀነስ መቻሉ ነው የተገለጸው።

ከዚህም በተጨማሪ በተጠኝዎች ላይ የስኳርና የኮሊስትሮል መጠንም ቀንሶ መታየቱ ተመላክቷል።

በዚሀም በተወሰኑ ሰዓት ብቻ በመመገብ፣ የምግብ አወሳሰድን በመቀነስ ላልተፈለገ የሰውነት ክብደት የተጋለጡና የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎችን ችግሮች እንደሚያቃልል ነው በዘገባው የተገለጸው።

ጥናቱ ቤሌሎች ተመራማሪዎች በዘርፉ ላይ ከተሰሩ የምርምር ውጤቶች ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን፦ በእየቀኑ መፆም ያልተፈለገ የሰውነት ክብደትንና የደም ግፊትን በመቀነስ ውጤታማ ነው ተብሏል።

የአሜሪካ በሽታዎች መከላከልና ቁጥጥር ማዕከል መረጃ እንደሚያመላክተው የሀገሪቱ አንድ ሶስተኛ ህዝብ ላልተፈለገ የሰውነት ክብደትና ተያያዥ ለሆኑ ‘‘የታይፕ’’ 2 የስኳር ፣ የልብና የደም ግፊት በሽታ ተጠቂ መሆኑን አመላክቷል።

 

 

ምንጭ፦ sciencedaily.com

የተተረጎመው፦ በእንቻለው ታደሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram