fbpx
AMHARIC

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስም ሀሰተኛ ሰነድ ተዘጋጅቶለት ወደ ሀገር ውስጥ የገባ ሁለት ኮንቴይነር ልባሽ ጨርቅ ተያዘ

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስም ሀሰተኛ ሰነድ ተዘጋጅቶለት የተመዘገበ በሁለት ኮንቴይነር የተጫነ ልባሽ ጨርቅ ወደ ሃገር ውስጥ ሲገባ ተያዘ።

ልባሽ ጨርቁን የጫነው ተሳቢ ወደ ሃገር ውስጥ ሲገባ የተያዘው ሎጊያ ላይ ነው ተብሏል።

የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የጋላፊ ቅርጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ አየለ ለፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ከትናንት በስቲያ ከለሊቱ 9 ሰዓት ጀምሮ በተደረገ ክትትልና ቁጥጥር ትናንት ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ሊያዝ ችሏል።

አቶ ተስፋዬ የንብረቱ ባለቤትነት እንዲሁም የተመዘገበውና የይለፍ ስርዓቱ የተፈጸመው በኢትየጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ቢሆንም ንብረቱን ያስገባው አካል ሌላ መሆኑን ገልጸዋል።

ፖሊስ አሽከርካሪውን በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን፥ አስመጪ አካሉን እንዲጠቁም ምርመራ እየተደረገበት ነው ተብሏል።

በተለያዩ ድርጅቶች ስም ሀሰተኛ ሰነዶች እየተዘጋጁ ሸቀጦች ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ስራ እየተበራከተ ነው የሚል ጥቆማ ለባለስልጣኑ መድረሱን ተከትሎ ለሶስት ወራት በተደረገ ክትትል እቃው በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉ ተመልክቷል።

 

 

በታሪክ አዱኛ – ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram