fbpx
AMHARIC

በኢራን ሴቶች ሀሰተኛ ጺም በማጥለቅ ለወንዶች ብቻ በተፈቀደ ስታዲየም ውስጥ ገብተው ጨዋታ ተከታተሉ

በኢራን ተጠባቂ የእግር ኳስ ግጥሚያ ለማየት ሴቶች ሰው ሰራሽ ጺም በማጥለቅ ለወንዶች ብቻ ወደ ተፈቀደ ስታዲየም በመግባት ጨዋታውን መከታተላቸውን ተገለጸ፡፡

በኢራን ሴቶች ስታዲየም ገብተው እግርኳስ እንዳይከታተሉ በህግ የታገዱ ሲሆን፥ ሴቶቹ የተቀመጠውን ህግ በመጣስ ነው ሜዳ የገቡት፡፡

በ2014 የብሪታንያና የኢራን ደም ያለባት ሴት የወንዶችን የቦሊ ቦል ጨዋታ ለመመልከት በመግባቷ ምክንያት ለአንድ ዓመት በእስር መቆየቷ ይታወሳል፡፡

እንዲሁም በዚህ ዓመት በተመሳሳይ ጨዋታ ለመከታተል የሞከሩ 35 ሴቶች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የኢራን ሴቶች መብት ተሟጋችና አቀንቃኝ የሆነችው ሜሎዲይ በሴቶቹ ድርጊት መኩራቷን ገልጻለች፡፡

እንዲሁም ፍርሃት የማያቃቸው ደፋሮች ነው ምክንያቱም የሚመጣባቸውን ችግር ተቋቁመው ነውና የገቡት ብላለች፡፡

ሜሎዲይ በሬጌ ዘፈኖቿ ወንዶች ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው የምታቀነቅን ሲሆን፥ በአሁኑ ሰዓት ኑሮዋን በዩናይትድ ስቴትስ አድርጋለች፡፡

እስከአሁን ሴቶች በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የተባለ ነገር የለም፡፡

ሳዑዲ አረቢያ ባለፈው ዓመት ሴቶች ወደ ስታዲየም ገብተው ጨዋታ እንዳይከታተሉ የሚለውን ህግ ያነሳችው ባለፈው ዓመት እንደነበር ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ኤስቢኤስ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram