fbpx
AMHARIC

በአዲስ አበባ ከ 1 ሺ 620 የግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ 707ቱ ክፍያ ሊጨምሩ ነው

~ 631 ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር ተወያይተውና ተደራድረው በዋጋ ላይ ተስማምተዋል፤

~ 23 ትምህርት ቤቶች በጭማሪው ከወላጆች ጋር አልተስማሙም፤

~ በከተማ አስተዳደሩ የግል ትምህርት ቤቶች ከመንግስት ትምህርት ቤቶች ከሶስት እጥፍ በላይ ይልቃሉ፤

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ 707 የግል ትምህርት ቤቶች ለመጪው የትምህርት ዓመት (2011) የትምህርት ክፍያ ለመጨመር ፖሮፖዛል ማስገባታቸውን የከተማ አስተዳደሩ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ሬጉላቶሪ ኤጀንሲ መግለጹን አዲስ ዘመን ጋዜጣ ዘገበ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 2 ሺ 89 ከቅድመ መደበኛ እስከ መሰናዶ ደረጃ ያሉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺ620ው የግል ትምህርት ቤቶች መሆናቸውን ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ትናንት (ግንቦት 7) በሰጠው መግለጫ ተናግሯል፡፡ ከቅድመ መደበኛ እስከ መሰናዶ ያሉ የመንግስት ትምህርት ቤቶችም 469 ብቻ መሆናቸው ታውቋል፡፡

በመግለጫው ወቅት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት ብሩክነሽ አርጋው እንደተናገሩት፤ በቀጣይ በጀት ዓመት የትምህርት ክፍያ ለመጨመር 707 የግል ትምህርት ቤቶች ፕሮፖዛል አስገብተዋል፡፡

ከእነዚህ ውስትም 631ዱ ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር ተወያይተውና ተደራድረው በዋጋ ላይ ተስማምተዋል፡፡ ከተቀሩት ውስጥ 23ቱ ደግሞ ከወላጅ ጋር መግባባት አልቻሉም፡፡

ፕሮፖዛል ካስገቡት 707 ትምህርት ቤቶች ውጪ ያሉት በቀድሞው ዋጋ የሚቀጥሉ ሲሆን፤ ዋጋ ለመጨመር ፕሮፖዛል ካስገቡት ውስጥ ከወላጅ ጋር ስምምነት ያልደረሱ ትምህርት ቤቶችን ጉዳይ ለመፍታትም ኤጀንሲው እንደሚሰራ ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ቢሮው ኃላፊ አቶ እንደሻው ጣሰው በበኩላቸው እንዳሉት፤ በከተማዋ ከቅድመ መደበኛ እስከ መሰናዶ ደረጃ ካሉ 2ሺ89 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1ሺ620ው የግል ትምህርት ቤቶች ናቸው፡፡

ቢሮውም ለመንግስትም ሆነ ለግል ትምህርት ቤቶች ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም የግል ትምህርት ቤቶች የሚያገለግሉት ህዝቡን መሆኑን አውቀው፤ በሚያደርጉት የዋጋ ጭማሪ ህብረተሰቡን ያማከለ ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

 

 

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram